Posts

የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ጫና

 ራሽያን ማዕቀብ ውስጥ ማቆየት ማንን ይጎዳል? አውሮፓውያን በተናጥል ከራሽያ ማዕቀብ ማዕቀፍ ውስጥ በከፊል አልያም በሙሉ መውጣት የሚጀምሩት ብዙም ሳይቆዩ አይመስላችሁም? ምክንያቱም ራሽያ መሰረታዊ የሚባለውን የአውሮፓ የገበያ ድርሻ በተለይ ነዳጅ፤ ማዳበሪያ፤ ብረት፤ ስንዴ፤ ወዘተ ላይ ተፅኖ አላት (ምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ከከፍተኛው 100% እስከ ዝቅተኛው 20% ድርሻቸው ከራሽያ ነው)። ስለዚህ በስሜት የሚያዘንቡት ማዕቀብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪም ኢኮኖሚያቸው ላይ የአቅርቦት እና የፍላጎት ክፍተት መፍጠሩን ከአሁኑ እየተመለከቱ ነው። ስለዚህ ሊያበቃለት ለሚችል የሶስተኛ ወገን ችግር ኢኮኖሚያቸው እንዲናጋ ለመፍቀድ ቅድሚያ ትንንሾቹ ሀገራት በመቀጠል ትልልቆቹ በጥልቀት ላይደፍሩ ይችላሉ። #ለምሳሌ፦ የራሽያ ባንኮችን ከስዊፍት ማገድ የገንዘብ ዝውውሮችን እና ኢንቨስትመንትን ሊጎዳ መቻሉን በመረዳት በአንዴ የተስማሙበት ማዕቀብ መሆን አይችልም (#ለምሳሌ፦ ጀርመን የዚህ አይነቱ ማዕቀብ እዳው ለጀርመንም መሆኑን በመረዳት ክርክር ላይ ነች)። ጦርነቱ ከፍቶ እና በሀይል ሚዛንነት ራሽያ ዩክሬንን ብታፈርሳት በዩክሬን ትከሻ የነበሩ ስንዴ፤ ብረት፤ የምግብ ዘይት፤ በቆሎ፤ ወዘተ በመሰረታዊነት የቀጠናው አምራች ሆና የምትቆየው ራሽያ ስለምትሆን ይህን ሁሉ ማጣት ቀላል ሊሆን አይችልም። ትናንት ሙሉ አውሮፓን በካርታ ላይ ያላቸውን ቅርበት፤ የየብስ (የቱቦ መስመርን ጨምሮ) እና የባህር የንግድ ቅርበት፤ የንግድ Trend እና ጥልፍልፎሽ ስመለከት የመጣልኝ ሃሳብ ይህ ነው።  #ለምሳሌ፦ በዚህ ወቅት ቻይና የስንዴ ምርት ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ክልከላዋን ለማንሳት እቅድ አላት! ስለዚህ የዓለም ገበያ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ብቻ ያለው ባለመሆኑ ቻይና ለነማን ቅድሚያ ትሰጣለች...
Image
 ❤️ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች ራስህን አታስጨንቅ። ❤️የጎደለህ ምንድን ነው?  ያለህስ ምንድን ነው ? ብታመዛዝነው የቱስ ይበልጣል?   መለወጥ የምትችላቸውን ዛሬ ጀምር። መለወጥ የማትችላቸውን ነገሮችን ግን ተቀበላቸው። ❤️አንዳንዴ ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው አታስመስል! ሌሎችን ለምምሰል በመጣር ራስህን አትጣ። ❤️ራስህን መሆን ነፃ ያድርጋል ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር። ራስህንም ከፍ ከፍ አድርገው እችላለሁ አደርገዋለሁ በል አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም!! በምትችለው ሰዎችን እርዳ,,,አመስጋኝ ሁን መልካም ሰዎችን አመስግናቸው። ሁሌም አዲስ ቀን ሲሰጥህ ፈጣሪህንም ማመስግን አትርሳ።
 ለውብ ቀን!     💛 ቢዝነስ እውቀት እንጂ ገንዘብ አይጠይቅም የቢዝነስ መነሻ እውቀት ነው፣ ጉጉት ነው፣ ጥረት ነው። በዚህ ዘመን ሀብት የማይጠይቁ ቢዝነሶች እየፈሉ ነው።  ሀብት የማይጠይቅ ቢዝነስ (Asset-Less Business) እውቀት ግን በደንብ ይጠይቃል። "እውቀት አለን" የሚሉ አንዳንዶች ገንዘብ አጥተን እንጂ ብዙ የምንሠራው ነበር ይላሉ፤ እውቀትና ገንዘብ አልተገናኘም ይላሉ። እኔ ግን አይመስለኝም። ገንዘብ ያለ እውቀት አይሠራም። እውቀት ያለው ሁሉ የእውቀቱ ማሳያ ሥራው ነው። ሥራው ደግሞ በስኬታማ ውጤት ሊታገዝ ግድ ነው። "እውቀት አለኝ" የሚል ሁሉ ለእውቀቱ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን እንደሚያቀርብ የታወቀ ነው። ከምስክር ወረቀት ይልቅ ሥራ ስለ እውቀት ሲመሰክር ግን ደስ ይላል፣ ያረካል። የምስክር ወረቀት ግን ተዓማኒነቱን ካጣ ሰነባበተ። ገሚሱ በፎርጅድ እያሠራ፣ ሌላው በገንዘብ እየገዛ፣ አንዳንዱም ኮርጆ እያለፈ፣ ሌላውም በለብ-ለብ የላይ የላይ እውቀት የምስክር ወረቀት ይዞ መታየቱ የተለመደ ሆኗል። ከልቡ ከአንጀቱ በቁም-ነገር የተማረውም ቢሆን ትምህርቱ የሰጠው እውቀት የራሱንም ይሁን የማህበረሰቡን ችግር ሲፈታ አይታይም። ለምን? አንዳንድ ካሬኩለሞች ጊዜ አልፎባቸዋል፤ አንዳንዶቹ ለዚህ አገር ችግር የታለሙ አይደሉም፣ ሌላም ሌላም ሌላም። ጥቂት መስኮች ብቻ ራሳቸውን ከዘመኑ ጋር እያስተካከሉ እየሄዱ ናቸው። ካለውም ይሁን ከመጪው ቴክኖሎጂ ጋር ራሳቸውን ያላዛመዱና ያላዘመኑ መስኮች ቀላል አይደሉም። ታድያ ምን ይሻላል? እንዴት ተምረን እንሻሻል? በሥራ ዓለም ነግደህ የምታተርፈው፣ ተቀጥረህ ጥሩ ደመወዝ የምታገኘው፣ ከሌሎች ተፎካካሪዎች በተሻለ ሁኔታ ችግር መፍታት ስትችል ነው። ከዚያ ውጪ ያለው መንገድ የማ...
 ከቃል በላይ ለእራስህ፣ ለህሊናህ ታመን! ፨፨፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዋናው ጉዳይ ማን ቃል ገባ የሚለው ሳይሆን ማን አብሮ ቆየ፣ ማን አዛለቀ፣ ማን ታመነ የሚለው ነው። ስንት ቃሉን እንደ እዳና እስር የሚቆጥር ባለበት ዘመን፣ ቃል ሳይገባ፣ መታሰሩን ሳይፈልገ ፍቅሩን ከቃልኪደን አስበልጦ አራሱን የሰጠ፣ ግፊትን ሳያሻ፣ ጫናን ሳይፈልግ በእራሱ የሚታመን ግሩም ሰው አለ። አዎ! ጀግኒት..! ቃልን እንደ እምነት እስር ከቆጠርሽው መቼም ልባዊ እምነትን አታገኚም። ማንም ሰው እስከጥግ የሚታመንልሽ ቃል ስለገባልሽ፣ በቃሉ ተገዶ ሳይሆን ስለሚወድሽ፣ ስለሚያፈቅርሽና ስለሚያከብርሽ ብቻ ነው። አዎ! ሰውን በቃል ሳይሆን በፍቅር እሰሪው፣ በግድ ሳይሆን በውድ አስገዢው፣ በጫና ሳይሆን በፍላጎቱ ማርኪው፤ ማንኛውም ሰው የሚያመዛዝን ህሊና አለው፣ የትኛው ትክክል የትኛው ስህተት እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። መታመን እንዳለበት ውስጡ ይነግረዋል፤ መቆጠብ እራሱን መወሰን እንዳለበት ያውቃል፤ አለመታመን ስሜቱን እንደሚጎዳ ያውቃል፤ ከቃል በላይ ህሊናው፣ ፍቅሩ እንደሚያስረው ነጋሪ አያሻውም፤ አዎ! ጀገናዬ..! ቃልን ማክበር፣ መታመን ከባድ ሆኖ አይደለም፣ ካልፈለገና ካላመነበት ግን ሳይከብደው በቀላሉ እምነቱን ያጣል፣ ቃሉን ያጥፋል፣ ስህተት መሆኑ እየገባው ስህተት ይሰራል። አዎ! በመታመንህ ወቅት እምነትህ ለሰው ሳይሆን ለእራስህ፣ ለገዛ ህሊናህ ነው። ላለመታመንህ ግዴታ ሌላ ከሳሽ አያስፈልግህም፣ ለወቀሳና ለትቺት የእራስህ ህሊና አያስቀምጥህም። ምናልባት በብዛቱ ልክ ህሊናህም ሊለምደውና ዝም ሊልህ ይችላል፣ ሲነሳ ግን ሊያጠፋህ እንደሚችል እወቅ። የጥፋተኝነት ስሜትን ማስቀረትም ሆነ ማጥፋት የምትችለው፦ ከቃልህ በላይ ለህሊናህ ስትታመን ነው፤ ከሰዎች ይልቅ ለእራ...
Image
 የደስታ ጉዳይ የደስታ ምንጮቹና መነሻዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ ደስታ ዘላቂ እንዲሆንና ትርጉም እንዲኖረው የሚያደርገው ግን አንድና አንድ ብቻ ነው! ምንም አደረግን ምንም ያደረግነውን ነገር ለሰው ካለን ፍቅርና ሰዎችን ለመጥቀም ካለን ፍላጎት ሲመነጭ ብቻ ደስታ ዘላቂ ይሆናል፡፡ የቀረው በሙሉ ጊዜያዊ ነው፡፡
Image
ስሜታችን ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ ነገሮች (“ገዢው ስሜት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) በስሜታችን ላይ ተጽእኖ ስላላቸው ነገሮች ስናስብ ምናልባት ሁኔታውን ከትናንትና፣ ከዛሬና ከነገ አንጻር ብናጤነው የጠራና ግልጽ እይታ ይኖረናል፡፡ ስሜታችን ከእውነታ ወይም ከእውነታ-መሰል ነገሮች ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ እውነታዎች ወይም እውነታ-መሰል ሁኔታዎች ደግሞ ካሳለፍነው፣ በማለፍ ላይ ካለነው ወይንም ደግሞ ወደፊት ይሆናል ብለን ከምናስበው ነገር ጋር ይነካካሉ፡፡ የስሜትን መንስኤዎች በዚህ መልኩ በትኖ መመልከቱ ስሜታችንን በሚገባ እንድንገነዘበው ይረዳናል፡፡ ይህ የስሜትን መንስኤ ከትናንቱ፣ ከዛሬውና ከነገው አንጻር ለማወቅ የምንጠቀምበት ሂደት ቀለል ያለው አቀራረብ ሲሆን፣ ምናልባት ሁኔታውን ከህክምናውና ሌሎች ጠለቅ ካሉ መንስኤዎች አንጻር ማየት የሚያስፈልግበትም ጊዜ እንዳለ አስታውሶ ማለፉ ተገቢ ነው፡፡ 1.  የትናንቱ - የስሜት መልህቆችና ትዝታዎች በስነ-ልቦናው አለም “መልህቆች” (Anchors) በመባል የሚታወቁ በስሜታችን ላይ ትልቅ ቦታ ያላቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች፣ እንደ ስእል፣ ድምጽ፣ ሽታና ጣእም የመሳሰሉ ከአንድ ስሜት ጋር ተቆራኝተው በውስጣችን ልክ እንደ መልህቅ ቸክለው የተቀመጡ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ አንድን ጣእም ስንቀምስ፣ ከዚያ ጣእም ጋር ተያይዞ በውስጣችን እንደተቀመጠው የስሜት “መልህቅ” አንጻር አንድ ደስ የሚል ወይም ደስ የማይል ስሜት ሊመጣ ይችላል፡፡ ስለዚህም ይህ ጣእም እንደ መልህቅ በውስጣችን በመተከልና በመቀመጥ በማንኛውም ሰዓት ያንን ስሜት ሊያመጣብን ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንዳንድ ሽታዎች፣ ድምጾችና አካባቢዎች እንደመልህቅ ሆነው የመተከልና ከአንድ ስሜት ጋር የመያያዝ ባህሪይ ...
 NATIONAL INTEREST የሩሲያን የሳይበር አቅም በሚገልፅበት ፅሁፉ አሜሪካን ከጥቅም ውጭ ለማድረግ የሚፈጅባቸው ጊዜ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ናቸው ይላል። ሩሲያ በአሜሪካ ላይ ከፍተኛ አቅማቸውን ተጠቅመው የሳይበር ጥቃት ቢፈፅሙ የአሜሪካን የኤሌክትሪክ ሃይል ቋቶችንና ወሳኝ የመሰረተልማት ተቋማትን ማለትም ኢንተርኔትን፣ የፋይናንስ ስርአቱን፣ የትራንስፖርት ሲስተሙን ፣ የምግብና ውሃ ማከፋፈያ ስርአትን፣ የመገናኛና የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶችን ከመቅፅበት ያወድሟቸዋል። ይህ የሩሲያ እጅግ የተራቀቀ የሳይበር አቅም ቢሰነዘር የአሜሪካን የቅድመ ጦር ማስጠንቀቂያ ሳይተላይቶችን ከጥቅም ውጪ ያደርጋቸዋል። ይህም በአሜሪካና በአጋሮቿ ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ምንም መረጃ የሌላቸው እውሮች ያደርጋቸውል። የአሜሪካ ጦር መሪዎች ይህንን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል ይላል። የአሜሪካው NATIONAL INTEREST መፅሔት የጦር መሪዎቹ በተደጋጋሚ በሰጡት ማስጠንቀቂያ " ከሩሲያ የሚፈፀምብን የሳይበር ጥቃት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻችንን እና ሲስተሞቹን እንዳንቆጣጠርና ማዘዝ እንዳንችል ልንደረግ እንችላለን " በማለት የኑክሌር ስርአቱ በነዚህ ሃይሎች ሊጠለፍ እንደሚችልም አሳስበዋል። የሩሲያ የሳይበር ጥቃት የአሜሪካን ፕሬዝዳንት የአፀፋ ኑክሌር ጥቃት እንዲፈፀም እንዳያዝ እንኳ ያደርገዋል። የአሜሪካ ጦር ከመሪዎቹ ጋር መነጋገር እንዳይችሉ ፤ መሪዎቹ ጦሩን ለማጥቃት እና መከላከል ማስተባበር እንዳይችሉና በዚህም በቀላሉ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል። አሜሪካ ደግሞ እንደዚህ ያሉ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችላትን ምንም አይነት Super Electromagnetic pulse (Super_EMP) አልታጠቀችም ሩሲያና ቻይና ግን የዚህ ባለቤት ናቸው። ሩሲያ የ Super-EMP ወይንም የሳይበር ጥ...
Image
 የናኖ ቴክኖሎጂ *********** ይህ አስገራሚ ዘርፍ የኢንጅነሪንግ፣ የሳንስና ቴክኖሎጂ ጥምረት ሲሆን መጣም ጥቃቅን ስለሆኑ ነገሮችም የሚያጠና ነው፡፡ ከ1-100 ናኖሜትር የሚደርስ መጠን ያላቸውን ትኩረት ያደርጋል፡፡ የዚህ ቴክኖሎጂ አባት እየተባለ የሚጠራው Richard Feynman ነው፡፡ የዚህ ሀሳብ ጥንስስ የተጀመረው በታህሳስ ወር 1959 የአሜሪካ የፊዚክስ ምሁራን ውይይት ጊዜ Richard Feynman ባነሳው “There’s Plenty of Room at the Bottom” በሚል ሀሳብ ነው፡፡ በውይቱ ፌይንማን እያንዳንዱን ሞሎኪዩልና አቶም እንዴት ነጣጥሎ ማጥናት እንደሚቻል አስረድቷል፡፡ ናኖ ቴክኖሎጂ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለማሰብ እጅግ በጣም ይከብዳል፡፡ አንድ ናኖ ሜትር አንድ ቢሊዮንኛ ሜትር ነው፡፡ በአንድ ኢንች ውስጥ 25,400,000 ያክል ናኖ ሜትሮች አሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ የጋዜጣ ወረቀት 100,000 ናኖ ምትር ውፍረት አለው፡፡ ተመራማሪዎች STM (scanning tunneling microscope) እና AFM (atomic force microscope) የሚባሉ ማይክሮስኮፖችን ከፈጠሩ በኋላ የናኖ ስኬል በሰፊው ስራ ላይ መዋል ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ይህ ቴክኖሎጂ በተለዩ መስኮች ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የፀሐይ መከላከያ ሎሽኖች (sunscreens) የተለያዩ የአይን መነጽሮች (Self-cleaning glass) አልባሳት እና ጸረ-ባክቴሪያ መጠቅለያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ምንጭ፡ National Nanotechnology Initiative  
 ✍️ ሰው እንደተወለደ የሚያለቅሰው ለምንድንነው?  አለኝ አንድ ወዳጄ :-  እኔሞ እንዲህ ስል መለስኩለት :: መወለድ ወደ ስቃይ መከራና ሰቆቃ መምጣት ነው:: መወለድ ስቃይን ማለፍ ነው መከራን መጋፈጥ ነው ሰቆቃን ታግሎ ድል መንሳት ነው::መወለድ ከአለመኖር ወደ መኖር መምጣት ነው:: መኖር ደግሞ ለህይወት ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ነው:: ለፈቃደ ስጋዊ ተግባር ሁሉ ተጠያቂ መሆን ነው:: ህይወት ጣዕም እንዲኖራት ጥሩ መዓዛ ያለውን የነፍስ የስጋና የፈቃድ ኡሁደት መፍጠር ነው::ይህን ማድረግ ደግሞ ብዙ ዳገት መውጣትንና ብዙ ቁልቁለት መውረድን የሚጠይቅ ነው:: ለዚህ ነው ወደምድር ስንመጣ የምናለቅሰው .....የወደፊቱን ስቃይ ፈተናና ወሰን የሌለውን በፍላጎት እሳት የምንቃጠለውን አመልካች ነው::        ቸር ሁኑ!!
 ✍️ ትክክለኛው መንገድ ላይ ሳትሆን መሮጥ ትርጉሙ ምንድን ነው? ሕይወት የእሽቅድድም መድረክ ነው:: በየፊናው ውድድር እና ጥሎ ማለፍ የሞላበት ክስተት ነው:: በትክክለኛው የህይወት ጎዳና ላይ ሳንሆን የምናደረገው እሽቅድድም ግን የማይረባና ትርጉም የሌለው ነው:: ውጤቱም ውድቀት ነው:: ምንም ያክል ረጅም ርቀት ቢኬድም መንገዱ ትክክለኛ ካልሆነ የተሻለ መፍትሄዉ መሮጥ ሳይሆን ወደኋላ መመለስ ነው:: መነሻዉ መድረሻውን የሚወሰነው የህይወት ሩጫ አለ:: ጅማሪው ትክክለኛው ካልሆነ ፍፃሜውም ስህተት ነው:: ለዚህ ደግሞ የተሻለ አማራጭ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን ሳናረጋግጥ አለመሮጥ ነው:: የትኛውንም ተግባራዊ እርምጃ ከማድረግ በፊት ማሰብ ማሰላሰል እና መመርመር ያስፈልጋል:: ጥልቅ በሆነ ማሰብና ማሰላሰል ውስጥ ህልውና ንቁ ይሆንና የሚደረገው ተግባራዊ እርምጃ ትክክል መሆን አለመሆኑን ያሳውቃል :: ይህን ሂደት አልፎ የሚከወን ተግባርም ሙሉ በሙሉ ከስህተት ባይፀዳም ትርጉም ያለው ይሆናል ::       ***ብሩህ ጊዜ🙏🙏🙏
 ✍️ በንፅህና መለኮት አንዴ ከተዋሃዳችሁ በህያውነት ዘለቀት ውስጥ ያለማቋረጥ እየጣፈጣችሁ ነው ማለት ነው:: ልክ ቡና ወተት ጋር ሲዋሃድ ማኪያቶ እንደሚሆነው....ከተዋሃደ በኋላ ወተቱን ከማኪያቶ መለየት እንደማይቻል ሁሉ ከፈጣሪ ንፅህና (ፍቅር:-እውነት) ጋር ስትዋሃዱ የህያውነት አካል ሆናችሁ ማለት ነውና ለፈጣሪ ልባችሁን በንፅህና ካሰናዳችሁ ፍቅር ተከስቶአል ሲከሰት ደግሞ ላይለያችሁ ተዋህዷል       🙏ንቃት🙏
 ✍️ ህይወት በየ ቅፅበት የምትገለጥ እንደ ጠብታ መጥፋትም መስፋትም የምትችል አዲስ ምዕራፍ ናት:: ትላንትን ኑረን አልፈናል ዛሬ ደግሞ ይህው ቀርቦልናል ህይወታችን በትላንት ስላልተወሰነ ዛሬ በአዲስ መልክ ቀርቧል::    ትዝታ ደግሞ ህይወትን ወደኋላ ለመጎትት የሚኮትን ሀይል ሁኖ ተደቅኗል :: በዚህ ሀይል ሳንታሰር ዛሬን በአግባብ እየኖርን ነገን የተሻለ እንዲሆን የምናልም ብቁ ሰው እንሁን!!
Image
 ምድርን ከአደጋ መጠበቅ ይፈልጋሉ ********************************** የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ያለንበትን የአየር ጠባይ ለውጥ እንደዋዛ መመልከት እንደማገባ በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡ የአየር ጠባይ ለውጡ በአለማችን ታይተው የማይታወቁ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ከማስከተሉም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ምርት ማነስን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የውሀ አካላት ከልካቸው በማለፍ በየአካባቢው የጎርፍ አደጋን እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ሀገራት ይህ የተፈጥሮ መናጋት ወደማይመለስበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት አስቸኳይ እርምጃን መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ መንግስታት መስራት ያለባቸውን እስኪሰሩ ድረስ እያንዳንዱ ሰው በግለሰብ ደረጃ የሚኖርባትን ምድር መንከባከብ የሚችልበትን መንገድ ከዚህ እንደሚከተለው ልናስነብባችሁ ወደድን፡፡ መልካም ንባብ 1ኛ. ውሃን በአግባቡ መጠቀም ስናያቸው ትንሽ ናቸው ብለን የምናስባቸው ነገሮች በትኩረት መሰራት ከቻሉ ትልቅ ለውጥ ማምታት ይችላሉ፡፡ በማንናውም ሰዓት ለምሳሌ ምሳ ለመብላት እጅ ስንታጠብ ወዲያው የመታጠቢያውን ውሀ መዝጋት ከቻልን እና ሌሎችም ይህን እንዲያደርጉ ከገፋፋን በቀላሉ የውሀ ብክነትን መቀነስ እንችላለን፡፡ በእርግጥ ውሃ የሚባክንበት ምክንያት ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን አንድን ነገር ለመስራት የሚያስፈልገንን ውሃ ብቻ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በተቻለ መጠን ውሀን ከቤታችን እያጣራን እንጠቀም፡፡ በዚህ ምክንያት ምድራችንን ከፕላስቲክ ኮዳዎች መታደግ እንችላለን፡፡ 2ኛ. መኪና የመጠቀም ልምዳችንን እንቀንስ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መኪና ይዞ መውጣት ጊዜያዊ የጤና ችግር ከማስከተሉ በተጨማሪ የካርቦን ልቀትን በማስፋፋት የተፈጥሮን ሚዛን ያዛባል፡፡ ከተቻለ ለ2 ቀን ከመኪና መንገድ ራቁ፡፡ መኪና መጠቀም ...
Image
 ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ይሕ Ethio Job Vacancy ነው። የወጣበት ቀን መስከረም 27/2013 ዓ.ም ምንጭ:- ሪፖርተር ጋዜጣ በሪፖርተር ጋዜጣ የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን ለማግኘት https://www.ethiopianreporterjobs.com ይጎብኙ መረጃውን #like  #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም ያካፍሉ። ሌሎችን የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ በሙሉ Please Join here.. www.facebook.com/groups/ethiojobvacancy/ Click here Blogger site https://oneethiopia1.blogspot.com/
Image
 የአፍንጫ መድማትን ለማቆም የሚያስችል መንገድ ******************************** ምንም እንኳን የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር አስደንጋጭ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የተለመደ ነው፡፡ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የአፍንጫ መድማት ይታይባቸዋል፡፡ በተለይ ከ2-10 ዕድሜ ክልል ያሉ ህፃናትና ከ50-80 ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ከፍተኛውን የቁጥር ድርሻ ይወስዳሉ፡፡    አፍንጫችን የምንስበውን አየር የሚያረጥቡ ብዙ የደም ስሮች አሉት፡፡ በአፍንጫችን በኩል የሚገባው አየርም ወደ አፍንጫችን ግድግዳ ተጠግቶ በሚያልፍበት ወቅት ለዚህ የመድማት ችግር ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው ከፍተኛ ግፊት ያለው ነፋስ ሲኖርና በእጃች አላስፈላጊ መነካካት ስናዘወትር ነው፡፡ እዚህ አካባቢ የሚከሰት መድማት anterior nosebleeds በመባል ይታወቃል፡፡ ብዙ ጊዜ ያልተለመደውና የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለው ከውስጠኛው የአፍንጫ ስር የሚመነጨው posterior nosebleeds የሚባለው ነው፡፡ ልዩ ህክምናም የሚስፈልገው የአፍንጫ መድማትም ይህኛው ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የአፍንጫ መድማት በአደጋ የአፍንጫ መሰበር ሲያጋጥም፣ የቅርብ ጊዜ የአፍንጫ ቀዶ ህክምና ሲኖር፣ ደምን ሊያቀጥኑ የሚችሉ መድሀኒቶችን ስንጠቀም፣ የደም ስሮችን የሚጎዳ ተፈጥሯዊ ችግር ሲኖርና የሉኪሚያ ተጠቂ ስንሆን የሚከሰት ነው፡፡ ይሁንና የአፍንጫ መድማትን በቀላሉ በቤት ውስጥ ማሰቆም ይቻላል፡፡ ችግሩን ለማስቆም ብዙ መንገዶች ቢኖሩም በአሜሪካ የሚገኘው Yale Medicine ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተሎች መከተል ተገቢ ነው ይላል፡፡   ተስተካክሎ በመቀመጥ የአፍንጫን ለስላሳውን ክፍል በለስላሳ ጨርቅ ወይም በሶፍት ለ10 ደቂቃ...
Image
 Never forget the hands that raised you !! ያሳደጉህን እጆች በጭራሽ አትርሳ !!  
Image
 💚ይቅር ባይ ሁን 💛 ዓለም በአዎንታዊና አሉታዊ ነገሮች የተሞላች ናት፡፡ ከአንድ መልካም ነገር ጎን ሌላ መጥፎ ነገር አለ፡፡ በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥም ሌላ መልካም ነገር ይገኛል፡፡ ❤️ከዚህም የተነሣ በሌሎች ሰዎች መገፋታችን ወይም እኛ ሰዎችን መግፋታችን አይቀርም፡፡ ይህ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕይወታችን ከሌሎች ጋር የተቋጠረና የተነካካ ነው፡፡ እኛነታችን ሌሎችን ይፈልጋል፡፡ እኛም ለሌሎች እናስፈልጋለን ፡፡ ሁሉም ሰው ከሌሎች የሚቀበለው ነገር አለው፡፡ ለሌሎች ሰጪም ነው፡፡ 💜 መሳሳት የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ዳሩ ግን መሳሳት የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም፡፡ ስህተት የእንቅስቃሴና የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ሰለዚህም መሳሳት በየትኛውም የሕይወት ገጽ ላይ ሊከሰት የሚችለው ፡፡ ❤️ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ መሳሳትና ማጥፋት አስቀያሚ ድክመት ነው፡፡ ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ ፡፡ ከተገፋንም በይቅርታ እንለፍ፡፡ ይህ የአእምሮ ብስለትና የመንፈስ ጥንካሬ ማሳያ ነው፡፡ ️❤️💛💜❤️💛💜❤️💛💜  
 የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም! ==================== (ሥነ-ልቦናዊ መፍትሔ) “በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቺያለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፊያለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቂያለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - ማይክል ጆርዳን። አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡ የዚህ አመለካከት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ሥነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡ የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት ...
Image
 ወረርሽኞችን እንዴት ማስቆም ይቻላል ************************************* አለማችን በልዩ ልዩ ወረርሽኞች ተጠቅታለች፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ተስፋችንን  በክትባቶች ላይ ብንጥልም እውነቱ ግን አብዘኞቹ ወረርሽኞች እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁ መሆኑ ነው፡፡ የጥንት ሰዎች ልክ እንዳሁኑ በተለያዩ ወረርሽኞች ተጠቅተዋል፡፡ ለምሳሌ The Black Death እየተባለ የሚጠራው ከ1346-1353 የተከሰተው ከሁሉም በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተከሰተው በልዩ ልዩ ጥናቶች እንደተመለከተው ለ2000 ዓመታት ያክል ወረርሽኝ ሆኖ የተከሰተው ምንጩ ባክቴሪያ የሆነው yersinia pestis ሌላው በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የወረርሽኞች የመስፋፋትና የገዳይነት አቅምም እየጨመረ መምጣቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ የሆንግ ኮንግ ጉንፋን እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ቢሆንም አሁንም ግን ስርጭቱ አላቆመም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት አስርት አመታት በፊት የተከሰተው ኤች አይ ቪ ቫይረስ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ስርጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እንደ WHO የቁጥር መረጃ ከሆነ በ2019 ብቻ በአለም ዙሪያ 690 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይዎታቸው አልፏል፡፡ ሌላም ሳርስ የተባለ ከ2002-2003 ብቻ 800 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን የቀጠፈ በሽታ በአለማችን መከሰቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ የሞት መጠኑ ያልታዎቀ በግማሽ አመት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ኮቪድ 19 ተከሰተ፡፡ በአጠቃላይ በአለማችን የተከሰቱ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ስንመለከት በቁጥጥር ስር ለመዋል ረጅም አመታትና ብዙ ትውልዶች ስፈልጓቸዋ...
Image
 የእይታ ችግር ላለባቸው ትልቅ መላ ********************************** ቺይኮ አሳካዋ ትባላለች፡፡ አይነ ስውር ናት፡፡ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ስትሆን በስራ ምክንያት በየወሩ ከአሜሪካ ጃፓን ከጃፓን አሜሪካ የአውሮፕላን ጉዞ ታደርጋለች፡፡ በረራ ያደረገችው ብቻዋን ከሆነ ከአየር መንገዱ ሰራተኞች አንዱ ወደምትፈልገው ቦታ ያደርሳታል፡፡ ካልሆነም የምትፈልገውን ሰው እስክታገኝ ለረጅም ሰዓት ትጠብቃለች፡፡ ችግር ብልሀትን ይወልዳል እንዲባል በዚህ ነገር የተማረረችው ቺይኮ ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሻንጣን ሰርታ አቅርባለች፡፡ ይህም ፈጠራዋ ከአውሮፕላን ከወረደች በኋላ በፍጥነትና ደህንነቷ እንደተጠበቀ ወደ መዳረሻዋ የሚመራት ነው፡፡ ሻንጣው የጉዞ ሻንጣ ሲሆን ካሜራና ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ ካሜራና ሴንሰሩ በአብዛኞቹ ራስ ነድ መኪኖች (autonomous car) እንደተገጠሙት ያለ ነው፡፡ ሻንጠው አካባቢውን እንዲያውቅ ሰው ሰራሽ ክህሎትን (artificial intelligence) ይጠቀማል፡፡ ሻንጣውን ለማዘዝ የሞባይል መተግበሪያ እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሻንጣው የሰው ፊት መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል፡፡ ይህም ተጠቃሚውንና በቅርብ ያለ ሰውን እንዲለይ ያስችለዋል፡፡ ይህች ድንቅ እንስት ሌሎች ብዙ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለአለም ያስተዋወቀች ሲሆን ከእነዚህም መካከል   "aDesigner," ለዲዛይነሮች የሚያግዝና ዌብሳቶችን ለተጠቃሚዎች ቀላል የሚያደርግ ቴክኖሎጂ፣ በድምጽ ኢንተርኔት መክፈት የሚያስችል በተለይ ለአይነ ስውራን ምቹ የሆነ ፈጠራ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ባለድንቅ ቴክኖሎጂውን ሻንጣ ለመስራት ያነሳሳትን ነገር ስትናገር " ብቻየን ስራመድ ምንም ምቾት አይሰማኝም፡፡ ሁልጊዜ በጉዞ ብቸኝነቴን ሊቀርፍል...