ከቃል በላይ ለእራስህ፣ ለህሊናህ ታመን!
፨፨፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዋናው ጉዳይ ማን ቃል ገባ የሚለው ሳይሆን ማን አብሮ ቆየ፣ ማን አዛለቀ፣ ማን ታመነ የሚለው ነው።
ስንት ቃሉን እንደ እዳና እስር የሚቆጥር ባለበት ዘመን፣ ቃል ሳይገባ፣ መታሰሩን ሳይፈልገ ፍቅሩን ከቃልኪደን አስበልጦ አራሱን የሰጠ፣ ግፊትን ሳያሻ፣ ጫናን ሳይፈልግ በእራሱ የሚታመን ግሩም ሰው አለ።
አዎ! ጀግኒት..! ቃልን እንደ እምነት እስር ከቆጠርሽው መቼም ልባዊ እምነትን አታገኚም። ማንም ሰው እስከጥግ የሚታመንልሽ ቃል ስለገባልሽ፣ በቃሉ ተገዶ ሳይሆን ስለሚወድሽ፣ ስለሚያፈቅርሽና ስለሚያከብርሽ ብቻ ነው።
አዎ! ሰውን በቃል ሳይሆን በፍቅር እሰሪው፣
በግድ ሳይሆን በውድ አስገዢው፣
በጫና ሳይሆን በፍላጎቱ ማርኪው፤
ማንኛውም ሰው የሚያመዛዝን ህሊና አለው፣ የትኛው ትክክል የትኛው ስህተት እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል።
መታመን እንዳለበት ውስጡ ይነግረዋል፤
መቆጠብ እራሱን መወሰን እንዳለበት ያውቃል፤
አለመታመን ስሜቱን እንደሚጎዳ ያውቃል፤
ከቃል በላይ ህሊናው፣ ፍቅሩ እንደሚያስረው ነጋሪ አያሻውም፤
አዎ! ጀገናዬ..! ቃልን ማክበር፣ መታመን ከባድ ሆኖ አይደለም፣ ካልፈለገና ካላመነበት ግን ሳይከብደው በቀላሉ እምነቱን ያጣል፣ ቃሉን ያጥፋል፣ ስህተት መሆኑ እየገባው ስህተት ይሰራል።
አዎ! በመታመንህ ወቅት እምነትህ ለሰው ሳይሆን ለእራስህ፣ ለገዛ ህሊናህ ነው።
ላለመታመንህ ግዴታ ሌላ ከሳሽ አያስፈልግህም፣ ለወቀሳና ለትቺት የእራስህ ህሊና አያስቀምጥህም። ምናልባት በብዛቱ ልክ ህሊናህም ሊለምደውና ዝም ሊልህ ይችላል፣ ሲነሳ ግን ሊያጠፋህ እንደሚችል እወቅ። የጥፋተኝነት ስሜትን ማስቀረትም ሆነ ማጥፋት የምትችለው፦
ከቃልህ በላይ ለህሊናህ ስትታመን ነው፤
ከሰዎች ይልቅ ለእራስህ ስትታመን ነው፤
ማንም ዘወትር አንተን የሚጠብቅ፣ እግር በእግር የሚቆጣጠር አካል የለም፤ ገዢህም፣ አዛዥህም የገዛ ህሊናህ ነው። ከእርሱ ያመለጥክ እንደሆነ ማቆሚያህ ከባድ ይሆናል፣
ማመዛዘን ትችላለህ፣
መምረጥ ትችላለህ፣
መወሰን፣ ማድረግ ትችላለህና ሁሌም በታማኝነት ተመላለስ፣ ቃል ካለህ ቃልህን ኑር እርሱን ባይኖርህም ህሊናህን አሳርፍ፣
አዎ! ከቃል በላይ ለእራስህ፣ ለህሊናህ ታመን! በጥቂቱ መታመንህ በብዙ ያሾምሃል፣ ትርፍህም ይበዛል፣ ሰላምህም ይፈካል፣ ፍቅርህም ያብባል።
ብሩህ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች