ምድርን ከአደጋ መጠበቅ ይፈልጋሉ
**********************************
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ያለንበትን የአየር ጠባይ ለውጥ እንደዋዛ መመልከት እንደማገባ በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡ የአየር ጠባይ ለውጡ በአለማችን ታይተው የማይታወቁ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ከማስከተሉም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ምርት ማነስን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የውሀ አካላት ከልካቸው በማለፍ በየአካባቢው የጎርፍ አደጋን እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ሀገራት ይህ የተፈጥሮ መናጋት ወደማይመለስበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት አስቸኳይ እርምጃን መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ መንግስታት መስራት ያለባቸውን እስኪሰሩ ድረስ እያንዳንዱ ሰው በግለሰብ ደረጃ የሚኖርባትን ምድር መንከባከብ የሚችልበትን መንገድ ከዚህ እንደሚከተለው ልናስነብባችሁ ወደድን፡፡ መልካም ንባብ
1ኛ. ውሃን በአግባቡ መጠቀም
ስናያቸው ትንሽ ናቸው ብለን የምናስባቸው ነገሮች በትኩረት መሰራት ከቻሉ ትልቅ ለውጥ ማምታት ይችላሉ፡፡ በማንናውም ሰዓት ለምሳሌ ምሳ ለመብላት እጅ ስንታጠብ ወዲያው የመታጠቢያውን ውሀ መዝጋት ከቻልን እና ሌሎችም ይህን እንዲያደርጉ ከገፋፋን በቀላሉ የውሀ ብክነትን መቀነስ እንችላለን፡፡ በእርግጥ ውሃ የሚባክንበት ምክንያት ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን አንድን ነገር ለመስራት የሚያስፈልገንን ውሃ ብቻ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በተቻለ መጠን ውሀን ከቤታችን እያጣራን እንጠቀም፡፡ በዚህ ምክንያት ምድራችንን ከፕላስቲክ ኮዳዎች መታደግ እንችላለን፡፡
2ኛ. መኪና የመጠቀም ልምዳችንን እንቀንስ
በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መኪና ይዞ መውጣት ጊዜያዊ የጤና ችግር ከማስከተሉ በተጨማሪ የካርቦን ልቀትን በማስፋፋት የተፈጥሮን ሚዛን ያዛባል፡፡ ከተቻለ ለ2 ቀን ከመኪና መንገድ ራቁ፡፡ መኪና መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ በአንድ ጉዞ ብዙ ተጋባራትን በመከወን ምልልሳችንን እንቀንስ፡፡



3ኛ. መራመድ፣ ብስክሌት መጠቀም፣ የህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም
በእግር መራመድና ብስክሌት መጠቀም ከተፈጥሮ ጋር ወደር የሌለው ስምምነት አላቸው፡፡ ካልሆነ ደግሞ የህዝብ ትራንስፖርን በመጠቀም በመንገድ ላይ የሚታዩ መኪኖችን ቁጥር በመቀነስ ሀላፍነትን መወጣት አስፈላጊ ነው፡፡
4ኛ. መቀነስ፣ በድጋሚ መጠቀምና ለሌላ አገልግሎት ማዋል
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ብክለትን በከፍተኛ መጠን መቀነስ ያቻላል፡፡ የተጠቀምናቸውን ነገሮች ከማስወገዳችን በፊት በድጋሚ መጠቀም መቻልና አለመቻላችንን ማረጋገጥ፡፡ በድጋሚ መጠቀም ከቻልን እናድርገው፡፡ ካልሆነ ደግሞ ወደሌላ አገልግሎት ለመቀየር ጥረት እናድርግ፡፡ ይህን በማድረግ የሚጣሉና በካይ የሆኑ ነገሮችን መቀነስ እንችላለን፡፡
5ኛ. ቆሻሻን ወደ ተፈጥሮ ማዳበሪያ መቀየር
መበስበስ የሚችሉ ውጋጆችን ጉድጓድ ቆፍሮ በመቅበር ወደተፈጥሮ ማዳበሪያነት መቀየር ይቻላል፡፡ ይህንም ማድረግ በሁለት መልኩ ይጠቅማል፡፡ የመጀመሪያው በአካባቢ የሚታይን ቆሻሻ ይቀንሳል፡፡ ሌላው ደግሙ ለሰብል ልማት የተፈጥሮ ማዳበሪያ የመጠቀም ልምድ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
6ኛ. የሐይል አጠቃቀምን ማስተካከል
የምንጠቀመው የቤት ውስጥ አምፖል የሀይል ፍላጎታችንን ይወስነዋል፡፡ በመሆኑም የቤት ውስጥ መገልገያዎቻችንን በሙሉ ሀይል ቆጣቢ በሆኑ መገልገያዎች በመተካት የሀይል ፍጆታችንን እንቀንስ፡፡ የሀይል ፍጆታን መቀነስ ለሀይል የምናወጣውን ወጭ ይቀንስልናል፡፡
7ኛ. ቤታችንን ማስተካከል
ቤታችን በቂ የሆነ ብርሀን የማያስገባ ከሆነ የሀይል ፍላጎታችን ሊጨምር ይችላል፡፡ ስለዚህ ቤትን በቂ ብርሀን እንዲያገኝ ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡


8ኛ. ለተፈጥሮ ምቹ የሆነ አመጋገብ
በተቻለ መጠን በምርት ሂደት መሬትን የማይጎዱ የግብርና ምርቶችን ለምግብነት መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በበለጠ ደግሞ የጓሮ አትክልትን በራስ አምረቶ መጠቀም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
9ኛ. ዛፎችን መትከልና መንከባከብ
በ2018 የተባበሩት መንግስታት በአየር ንብረት ዙሪያ የሚሰራ የመንግስታት ጥምረት ባወጣው ሪፖርት በ2050 የተለያ ብዛት ያላቸው የተለያዩ የዛፍ ዝርያዎች መተከል አለባቸው ብሎ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በሀገራችንም በዚሁ ረገድ አበረታች ስራ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደ ግለሰብ ግን በአመት ቢያንስ ሁለት ዛፎችን ተክለን ተንከባክበን ብናጸድቅ የሚመጣውን ለውጥ መገመት ቀላል ነው፡፡
10ኛ. ፕላስቲክን አለመጠቀም
ይህ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም በተፈጥሮ ላይ የሚያመጣው ቀውስ ግን በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ፕላስቲክን ለመገልገያነት ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ለአንድና ሁለት ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ፕላስቲኮችን ባለመጠቀም ብድራችንን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ማላቀቅ ይኖርብናል፡፡
እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን 10 ነገሮች ሁሉም የአለም ህዝብ መተግበር ቢችል ምድራችን እንዴት ጤናማ ትሆን ይለናል ከwww.howstuffworks ያገኘነው መረጃ፡፡


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች