Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps March 03, 2022 የደስታ ጉዳይየደስታ ምንጮቹና መነሻዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ ደስታ ዘላቂ እንዲሆንና ትርጉም እንዲኖረው የሚያደርገው ግን አንድና አንድ ብቻ ነው! ምንም አደረግን ምንም ያደረግነውን ነገር ለሰው ካለን ፍቅርና ሰዎችን ለመጥቀም ካለን ፍላጎት ሲመነጭ ብቻ ደስታ ዘላቂ ይሆናል፡፡ የቀረው በሙሉ ጊዜያዊ ነው፡፡ Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች August 30, 2019 የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች.....#share *ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ ነቢይ በሀገሩ አይከበርም። *መዐር አይጥዕሞ ለአድግ ለአህያ ማር አይጥማትም *አድኅን ርእስከ ራስህን አድን *አፍ ይጼውአ ለሞት አፍ ሞትን ይጠራል *ለሰሚዕ እጽብ ለሰሚው አስደናቂ *ብላዕ በሐፈ ገጽከ ጥረህ ግረህ ብላ *አክብር አባከ ወእመከ አባትና እናትህን አክብር *ተፋቀሩ በበይናቲከሙ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ *ኀላፊ ንብረት፣ክመ ጽላሎት ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው *እምነ ረሃብ የኄይስ ኩይናት ከረሀብ ጦርነት ይሻላል። *ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል ለሚያምን ሁሉ ይቻላል *ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ ያይን በሽታዋ ጠላትን ማየቷ *እለ ከርሦሙ አምላኮሙ ሆድ አምላኪዎች *ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለከ ለለመነህ ሁሉ ስጥ *በቁስለ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን *አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ ለሮጠ አይደለም ለቀደመ እንጅ *አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ *እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት። *ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ *መኑ ከመ አምላከነ? እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ? *አኮ በሲበት አላ በአእምሮ በሽበት አይደለም፤በማስተዋል እንጅ *ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ *ሀቡ ዘነጋሢ ለነጋሢ፤ወዘተረፈእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር፤የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ። ... Read more
ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው August 27, 2019 ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው ስንል ይኸው በማስረጃ ነው። ጥንታዊቷ ፊደላችን ♥ አ ቦ ጊ ዳ ................ የኢትዮጵያ ታሪክ ቅርስ በዓለም ሁሉ የአበራ የተመዘገበ ነው እኛ የእኛውን ሀብታችን እንጠብቅ።ትንሽ ስለአማርኛ ቋንቋ ... መራራ ሃቅ 1. የአማርኛ ቋንቋ ከክርስቶስ ልደት በፊት ነበረ። በሁለተኛው ክፍለ ዘመን (200-130 ዓ . ዓ ) የግብጹ ንጉሥ ጥሊሞስ 7 ኛ መምህር የነበረውና የግሪክ መልክዓ ምድር ተመራማሪ አጋታርከስ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦች የሚናገሩት የአማርኛ ቋንቋ እንደሆነ ጽፏል፥ተረጋግጧል።በአርኪኦሎጂያዊ ምርመራ ሂደት በአማርኛ የተቀረጹ ጥንታዊ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ተገኝተዋል ( አምሳሉ 1976) 2. አማራዎች ከ 3 ሺህ አመት በፊት በአማርኛ ቋንቋ ለንግሥት ሳባ ልጅ " ምኒልክ " ብለው ስም ከአወጡ በኋላ ይሁን በፊት በርካታ ስሞችን በአማርኛ እናገኛለን። 3. አሜሪካዊው ቤንደር በ 1966 ዓ . ም በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ባሳተመው /Language in Ethiopia/ በሚሰኘው መፅሐፉ በ 9 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አማርኛ በቤተ - አምሓራ እንደተስፋፋ ጽፏል።ኩፐር የተባለው ጽሐፊ በንጉስ ላሊበላ ዘመን አማርኛ ከአገወኛ ጋር በህዝቡ ይነገር ነበር ብሏል። 4. በ 12 ኛው መክዘ አጼ ይኩኖ አምላክ ዘመን ዐማርኛ ቋንቋ ፈጽሞ ሠለጠነ ፤ ያማረ የተወደደ ፥ ጉሮሮ የማያንቅ ፥ ለንግግር የማያውክ ሁኖ ስለ ተገኘ ፣ የቤተ መንግሥት ቋንቋ ሆነ።ለአማርኛ ዕድገት የ... Read more
October 02, 2020 ሕዝቤማ ጀግና ነህ ! ትመግበው ማያይልቅ... ታጠጣው የማይደርቅ... ከደረቅ አፈር ስር፣ ሕይወት ምግብ ሠሪ፤ በተረሳ ቀየህ... ከተፈጥሮ ታግለህ፣ ትርፍ አምርቶ ኗሪ፤ ሀገር ክብር ነስታህ... ሀገር ገንብቶ ሟች፣ አልፎ አ ሻ ጋ ሪ። ከፍታህን የሚያክል፣ አንተን የሚመጥን፣ አጥተህ እንጂ መሪ፤ ሕዝቤማ ታላቅ ነህ... ትመስክር ይች ምድር፣ ይመስክር ፈጣሪ!!! Read more
Comments
Post a Comment