✍️ ሰው እንደተወለደ የሚያለቅሰው ለምንድንነው? 

አለኝ አንድ ወዳጄ :- 

እኔሞ እንዲህ ስል መለስኩለት ::
መወለድ ወደ ስቃይ መከራና ሰቆቃ መምጣት ነው:: መወለድ ስቃይን ማለፍ ነው መከራን መጋፈጥ ነው ሰቆቃን ታግሎ ድል መንሳት ነው::መወለድ ከአለመኖር ወደ መኖር መምጣት ነው::
መኖር ደግሞ ለህይወት ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ነው:: ለፈቃደ ስጋዊ ተግባር ሁሉ ተጠያቂ መሆን ነው::
ህይወት ጣዕም እንዲኖራት ጥሩ መዓዛ ያለውን የነፍስ የስጋና የፈቃድ ኡሁደት መፍጠር ነው::ይህን ማድረግ ደግሞ ብዙ ዳገት መውጣትንና ብዙ ቁልቁለት መውረድን የሚጠይቅ ነው::
ለዚህ ነው ወደምድር ስንመጣ የምናለቅሰው .....የወደፊቱን ስቃይ ፈተናና ወሰን የሌለውን በፍላጎት እሳት የምንቃጠለውን አመልካች ነው::
       ቸር ሁኑ!!

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች