NATIONAL INTEREST የሩሲያን የሳይበር አቅም በሚገልፅበት ፅሁፉ አሜሪካን ከጥቅም ውጭ ለማድረግ የሚፈጅባቸው ጊዜ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ናቸው ይላል። ሩሲያ በአሜሪካ ላይ ከፍተኛ አቅማቸውን ተጠቅመው የሳይበር ጥቃት ቢፈፅሙ የአሜሪካን የኤሌክትሪክ ሃይል ቋቶችንና ወሳኝ የመሰረተልማት ተቋማትን ማለትም ኢንተርኔትን፣ የፋይናንስ ስርአቱን፣ የትራንስፖርት ሲስተሙን ፣ የምግብና ውሃ ማከፋፈያ ስርአትን፣ የመገናኛና የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶችን ከመቅፅበት ያወድሟቸዋል።

ይህ የሩሲያ እጅግ የተራቀቀ የሳይበር አቅም ቢሰነዘር የአሜሪካን የቅድመ ጦር ማስጠንቀቂያ ሳይተላይቶችን ከጥቅም ውጪ ያደርጋቸዋል። ይህም በአሜሪካና በአጋሮቿ ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ምንም መረጃ የሌላቸው እውሮች ያደርጋቸውል።

የአሜሪካ ጦር መሪዎች ይህንን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል ይላል። የአሜሪካው NATIONAL INTEREST መፅሔት የጦር መሪዎቹ በተደጋጋሚ በሰጡት ማስጠንቀቂያ " ከሩሲያ የሚፈፀምብን የሳይበር ጥቃት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻችንን እና ሲስተሞቹን እንዳንቆጣጠርና ማዘዝ እንዳንችል ልንደረግ እንችላለን " በማለት የኑክሌር ስርአቱ በነዚህ ሃይሎች ሊጠለፍ እንደሚችልም አሳስበዋል።

የሩሲያ የሳይበር ጥቃት የአሜሪካን ፕሬዝዳንት የአፀፋ ኑክሌር ጥቃት እንዲፈፀም እንዳያዝ እንኳ ያደርገዋል። የአሜሪካ ጦር ከመሪዎቹ ጋር መነጋገር እንዳይችሉ ፤ መሪዎቹ ጦሩን ለማጥቃት እና መከላከል ማስተባበር እንዳይችሉና በዚህም በቀላሉ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል።

አሜሪካ ደግሞ እንደዚህ ያሉ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችላትን ምንም አይነት Super Electromagnetic pulse (Super_EMP) አልታጠቀችም ሩሲያና ቻይና ግን የዚህ ባለቤት ናቸው። ሩሲያ የ Super-EMP ወይንም የሳይበር ጥቃት አሜሪካ ላይ ብትፈፅም አሜሪካ ያላት 94 የኑክሌር ማብላያ ጣቢያዎች በደቂቃዎች ውስጥ ይቀልጣሉ ይወድማሉ።

ይህም የradioactive አደገኛ ጨረሮችን ወደከተሞች ይለቃል። ይህ ጥቃት ቢፈፀም የአሜሪካ መሪዎች ማን ጥቃቱን እንደፈፀመባቸውም ሆነ ማንን መበቀል እንዳለባቸው አያውቁም። ይህም የአሜሪካን ህልውና እንዲያከትም ያደርገዋል ነው ተረኩ።

ሩሲያ በአሜሪካ ላይ የሳይበር ጥቃት መፈፀም ከጀመረች የቆየች ሲሆን አሜሪካ በአፀፋው በሩሲያ ላይ የሳይበር ጥቃት መፈፀም አልቻለችም። የአሜሪካን ምርጫ ጠልፋ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፍ እስከማድረግ የቻለችው ሩሲያ አሜሪካን ማንበርከክ የሚችሉ የሳይበር ቴክኖሎጂዎችን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች ትገኛለች።

እናም የነዚህ ሀገራት የሳይበር ቴክኖሎጂ በዚህ ያክል ረቂቅነት ከዘመነ እያንዳንዱ ሀገር ያለውን ከኑክሌር እስከ ሚሳኤል መሳሪያ መቆጣጠርና ማዘዝ እንዳይችል ከማድረጉም በላይ በራሳቸው የታጠቁት ኑክሌር መጥፊያቸው እንዲሆን የሚያደርግ ነው ይላሉ። ለዚህም ነው የሳይበር ጦርነት ተወዳዳሪ የሌለው እጅግ አውዳሚው ጦርነት ይሆናል የሚባለው። 🇷🇺🇷🇺🇷🇺

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች