የናኖ ቴክኖሎጂ
***********
ይህ አስገራሚ ዘርፍ የኢንጅነሪንግ፣ የሳንስና ቴክኖሎጂ ጥምረት ሲሆን መጣም ጥቃቅን ስለሆኑ ነገሮችም የሚያጠና ነው፡፡ ከ1-100 ናኖሜትር የሚደርስ መጠን ያላቸውን ትኩረት ያደርጋል፡፡ የዚህ ቴክኖሎጂ አባት እየተባለ የሚጠራው Richard Feynman ነው፡፡ የዚህ ሀሳብ ጥንስስ የተጀመረው በታህሳስ ወር 1959 የአሜሪካ የፊዚክስ ምሁራን ውይይት ጊዜ Richard Feynman ባነሳው “There’s Plenty of Room at the Bottom” በሚል ሀሳብ ነው፡፡ በውይቱ ፌይንማን እያንዳንዱን ሞሎኪዩልና አቶም እንዴት ነጣጥሎ ማጥናት እንደሚቻል አስረድቷል፡፡
ናኖ ቴክኖሎጂ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለማሰብ እጅግ በጣም ይከብዳል፡፡ አንድ ናኖ ሜትር አንድ ቢሊዮንኛ ሜትር ነው፡፡ በአንድ ኢንች ውስጥ 25,400,000 ያክል ናኖ ሜትሮች አሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ የጋዜጣ ወረቀት 100,000 ናኖ ምትር ውፍረት አለው፡፡
ተመራማሪዎች STM (scanning tunneling microscope) እና AFM (atomic force microscope) የሚባሉ ማይክሮስኮፖችን ከፈጠሩ በኋላ የናኖ ስኬል በሰፊው ስራ ላይ መዋል ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ይህ ቴክኖሎጂ በተለዩ መስኮች ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የፀሐይ መከላከያ ሎሽኖች (sunscreens) የተለያዩ የአይን መነጽሮች (Self-cleaning glass) አልባሳት እና ጸረ-ባክቴሪያ መጠቅለያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ምንጭ፡ National Nanotechnology Initiative


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች