የእይታ ችግር ላለባቸው ትልቅ መላ
**********************************
ቺይኮ አሳካዋ ትባላለች፡፡ አይነ ስውር ናት፡፡ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ስትሆን በስራ ምክንያት በየወሩ ከአሜሪካ ጃፓን ከጃፓን አሜሪካ የአውሮፕላን ጉዞ ታደርጋለች፡፡ በረራ ያደረገችው ብቻዋን ከሆነ ከአየር መንገዱ ሰራተኞች አንዱ ወደምትፈልገው ቦታ ያደርሳታል፡፡ ካልሆነም የምትፈልገውን ሰው እስክታገኝ ለረጅም ሰዓት ትጠብቃለች፡፡
ችግር ብልሀትን ይወልዳል እንዲባል በዚህ ነገር የተማረረችው ቺይኮ ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሻንጣን ሰርታ አቅርባለች፡፡ ይህም ፈጠራዋ ከአውሮፕላን ከወረደች በኋላ በፍጥነትና ደህንነቷ እንደተጠበቀ ወደ መዳረሻዋ የሚመራት ነው፡፡ ሻንጣው የጉዞ ሻንጣ ሲሆን ካሜራና ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ ካሜራና ሴንሰሩ በአብዛኞቹ ራስ ነድ መኪኖች (autonomous car) እንደተገጠሙት ያለ ነው፡፡ ሻንጠው አካባቢውን እንዲያውቅ ሰው ሰራሽ ክህሎትን (artificial intelligence) ይጠቀማል፡፡ ሻንጣውን ለማዘዝ የሞባይል መተግበሪያ እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሻንጣው የሰው ፊት መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል፡፡ ይህም ተጠቃሚውንና በቅርብ ያለ ሰውን እንዲለይ ያስችለዋል፡፡
ይህች ድንቅ እንስት ሌሎች ብዙ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለአለም ያስተዋወቀች ሲሆን ከእነዚህም መካከል   "aDesigner," ለዲዛይነሮች የሚያግዝና ዌብሳቶችን ለተጠቃሚዎች ቀላል የሚያደርግ ቴክኖሎጂ፣ በድምጽ ኢንተርኔት መክፈት የሚያስችል በተለይ ለአይነ ስውራን ምቹ የሆነ ፈጠራ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ባለድንቅ ቴክኖሎጂውን ሻንጣ ለመስራት ያነሳሳትን ነገር ስትናገር " ብቻየን ስራመድ ምንም ምቾት አይሰማኝም፡፡ ሁልጊዜ በጉዞ ብቸኝነቴን ሊቀርፍልኝ የሚችል ቴክኖሎጂ ምን ሊሆን ይችላል እያልኩ አስባለሁ፡፡ እንዲሁም ስጓዝ የደህንነት ስሜት እንዲሰማኝና በፍጥነት እንዲሆን እፈልጋለሁ ይህም ነው ይህን ሻንጣ እንድሰራ መነሻ የሆነኝ" ትላለች፡፡ ሻንጣው ሌሎች አይነ ስውራንን ሊያግዙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለታል፡፡
ምንጫ CNN Travel


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች