✍️ ትክክለኛው መንገድ ላይ ሳትሆን መሮጥ ትርጉሙ ምንድን ነው?
ሕይወት የእሽቅድድም መድረክ ነው:: በየፊናው ውድድር እና ጥሎ ማለፍ የሞላበት ክስተት ነው::
በትክክለኛው የህይወት ጎዳና ላይ ሳንሆን የምናደረገው እሽቅድድም ግን የማይረባና ትርጉም የሌለው ነው::
ውጤቱም ውድቀት ነው::
ምንም ያክል ረጅም ርቀት ቢኬድም መንገዱ ትክክለኛ ካልሆነ የተሻለ መፍትሄዉ መሮጥ ሳይሆን ወደኋላ መመለስ ነው::
መነሻዉ መድረሻውን የሚወሰነው የህይወት ሩጫ አለ::
ጅማሪው ትክክለኛው ካልሆነ ፍፃሜውም ስህተት ነው::
ለዚህ ደግሞ የተሻለ አማራጭ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን ሳናረጋግጥ አለመሮጥ ነው:: የትኛውንም ተግባራዊ እርምጃ ከማድረግ በፊት ማሰብ ማሰላሰል እና መመርመር ያስፈልጋል::
ጥልቅ በሆነ ማሰብና ማሰላሰል ውስጥ ህልውና ንቁ ይሆንና የሚደረገው ተግባራዊ እርምጃ ትክክል መሆን አለመሆኑን ያሳውቃል ::
ይህን ሂደት አልፎ የሚከወን ተግባርም ሙሉ በሙሉ ከስህተት ባይፀዳም ትርጉም ያለው ይሆናል ::
      ***ብሩህ ጊዜ🙏🙏🙏

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች