ለውብ ቀን!
💛
ቢዝነስ እውቀት እንጂ ገንዘብ አይጠይቅም
የቢዝነስ መነሻ እውቀት ነው፣ ጉጉት ነው፣ ጥረት ነው። በዚህ ዘመን ሀብት የማይጠይቁ ቢዝነሶች እየፈሉ ነው። ሀብት የማይጠይቅ ቢዝነስ (Asset-Less Business) እውቀት ግን በደንብ ይጠይቃል።
"እውቀት አለን" የሚሉ አንዳንዶች ገንዘብ አጥተን እንጂ ብዙ የምንሠራው ነበር ይላሉ፤ እውቀትና ገንዘብ አልተገናኘም ይላሉ። እኔ ግን አይመስለኝም። ገንዘብ ያለ እውቀት አይሠራም።
እውቀት ያለው ሁሉ የእውቀቱ ማሳያ ሥራው ነው። ሥራው ደግሞ በስኬታማ ውጤት ሊታገዝ ግድ ነው።
"እውቀት አለኝ" የሚል ሁሉ ለእውቀቱ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን እንደሚያቀርብ የታወቀ ነው። ከምስክር ወረቀት ይልቅ ሥራ ስለ እውቀት ሲመሰክር ግን ደስ ይላል፣ ያረካል። የምስክር ወረቀት ግን ተዓማኒነቱን ካጣ ሰነባበተ።
ገሚሱ በፎርጅድ እያሠራ፣ ሌላው በገንዘብ እየገዛ፣ አንዳንዱም ኮርጆ እያለፈ፣ ሌላውም በለብ-ለብ የላይ የላይ እውቀት የምስክር ወረቀት ይዞ መታየቱ የተለመደ ሆኗል።
ከልቡ ከአንጀቱ በቁም-ነገር የተማረውም ቢሆን ትምህርቱ የሰጠው እውቀት የራሱንም ይሁን የማህበረሰቡን ችግር ሲፈታ አይታይም። ለምን?
አንዳንድ ካሬኩለሞች ጊዜ አልፎባቸዋል፤ አንዳንዶቹ ለዚህ አገር ችግር የታለሙ አይደሉም፣ ሌላም ሌላም ሌላም። ጥቂት መስኮች ብቻ ራሳቸውን ከዘመኑ ጋር እያስተካከሉ እየሄዱ ናቸው። ካለውም ይሁን ከመጪው ቴክኖሎጂ ጋር ራሳቸውን ያላዛመዱና ያላዘመኑ መስኮች ቀላል አይደሉም።
ታድያ ምን ይሻላል? እንዴት ተምረን እንሻሻል?
በሥራ ዓለም ነግደህ የምታተርፈው፣ ተቀጥረህ ጥሩ ደመወዝ የምታገኘው፣ ከሌሎች ተፎካካሪዎች በተሻለ ሁኔታ ችግር መፍታት ስትችል ነው። ከዚያ ውጪ ያለው መንገድ የማጭበርበርና የሌብነት መንገድ ነው።
ከሌሎች በተሻለ ሁኔታ ችግር ለመፍታት ምን ያስፈልጋል? የሚያስፈልገው የተሻለ እውቀት፣ ክህሎት፣ ልምድ፣ አመለካከት፣ መልካም ግንኙነት፣ ተግባቦት፣ የማስተባበርና የመምራት ችሎታ እና ጊዜና ወጪ ቆጣቢነት ነው።
ለዚህ የሚያበቁ ስልጠናዎችን ወስደህ ችግር መፍታት ከቻልህ ጦምህን አታድርም። ጦም ማደርን ከማሸነፍም በላይ ተፈላጊነትህ ይጨምራል፤ ገበያህ ይደራል። በሥራ ላይ ሥራ፣ በገበያ ላይ ገበያ ታገኛለህ። You become OVERSUBSCRIBED.
ንብረት የማይጠይቁ፣ ማስያዣ የማይጠይቁ ቢዝነሶች ሞልተዋል። እነዚያ ቢዝነሶች ግን እውቀት፣ ክህሎት፣ ልምድ፣ ተግባቦት፣... ይጠይቃሉ።
ለምሳሌ:- ጥሩ ሻጭ ከሆንክ በባትሪ ፈልገው ያሠሩሃል፣ ጥሩ ኮስት አካውንታንት፣ ጥሩ ማኔጀር ከሆንክም እንደዚያው። ጥሩ ዳቦና ኬክ ጋጋሪ ከሆንክም ዞር ዞር እያልክ መሥራትህ የተለመደ ነው። ጥሩ የስፌት መኪና መካኒኮች ሁሌም በህመም ፈቃድ አሳብበው ከድርጅት ድርጅት እየዞሩ የመሥራታቸው ምስጢር ይህ ነው። They are Oversubscribed.
ባለችሎታና የጣት ወርቅ አንድ ነው
ሹልክ ያለ እንደሆን ፈላጊው ብዙ ነው
የሚባለው ያለምክንያት አይደለም። በል እንግዲህ የጣት ወርቅ ለመሆን ተጣጣር፣ ራስህን አሰልጥን። እናም ተፈላጊነትህን ጨምር። Become oversubscribed. Thanks God, I invested a lot of time and effort to build myself and now I am oversubscribed.
Becoming oversubscribed requires a lot of effort. It requires continuous effort to update yourself. Update yourself with necessary trainings. Pay your dues on continuous basis.
በዚህ ዘመን የምስክር ወረቀት (Certification) አምነው የሚቀጥሩ የዋሆች ናቸው፤ በሰው ጥቆማ (Recommendation) የሚቀጥሩ ግን ብልሆች ናቸው። I recommend.
The age of certification has passed. It is the age of recommendation.
እውቀት ኖሮህ ለራስህ መሥራት ከፈለግህም መነሻ ሀብት የማይጠይቁ ብዙ የሥራ መስኮች አሉ። ፈልግና አግኛቸው።
የምታውቃቸው Asset-less businesses የትኞቹ ናቸው? አስተማማኝነታቸውን ፈትሽ ወይ አስፈትሽ። ቢዝነስ ለብቻ እንደማይሠራም ልብ በል።
Popular posts from this blog
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች.....#share *ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ ነቢይ በሀገሩ አይከበርም። *መዐር አይጥዕሞ ለአድግ ለአህያ ማር አይጥማትም *አድኅን ርእስከ ራስህን አድን *አፍ ይጼውአ ለሞት አፍ ሞትን ይጠራል *ለሰሚዕ እጽብ ለሰሚው አስደናቂ *ብላዕ በሐፈ ገጽከ ጥረህ ግረህ ብላ *አክብር አባከ ወእመከ አባትና እናትህን አክብር *ተፋቀሩ በበይናቲከሙ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ *ኀላፊ ንብረት፣ክመ ጽላሎት ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው *እምነ ረሃብ የኄይስ ኩይናት ከረሀብ ጦርነት ይሻላል። *ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል ለሚያምን ሁሉ ይቻላል *ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ ያይን በሽታዋ ጠላትን ማየቷ *እለ ከርሦሙ አምላኮሙ ሆድ አምላኪዎች *ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለከ ለለመነህ ሁሉ ስጥ *በቁስለ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን *አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ ለሮጠ አይደለም ለቀደመ እንጅ *አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ *እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት። *ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ *መኑ ከመ አምላከነ? እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ? *አኮ በሲበት አላ በአእምሮ በሽበት አይደለም፤በማስተዋል እንጅ *ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ *ሀቡ ዘነጋሢ ለነጋሢ፤ወዘተረፈእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር፤የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ። ...
❤️ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች ራስህን አታስጨንቅ። ❤️የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ? ብታመዛዝነው የቱስ ይበልጣል? መለወጥ የምትችላቸውን ዛሬ ጀምር። መለወጥ የማትችላቸውን ነገሮችን ግን ተቀበላቸው። ❤️አንዳንዴ ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው አታስመስል! ሌሎችን ለምምሰል በመጣር ራስህን አትጣ። ❤️ራስህን መሆን ነፃ ያድርጋል ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር። ራስህንም ከፍ ከፍ አድርገው እችላለሁ አደርገዋለሁ በል አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም!! በምትችለው ሰዎችን እርዳ,,,አመስጋኝ ሁን መልካም ሰዎችን አመስግናቸው። ሁሌም አዲስ ቀን ሲሰጥህ ፈጣሪህንም ማመስግን አትርሳ።
Comments
Post a Comment