የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ጫና
ራሽያን ማዕቀብ ውስጥ ማቆየት ማንን ይጎዳል?
አውሮፓውያን በተናጥል ከራሽያ ማዕቀብ ማዕቀፍ ውስጥ በከፊል አልያም በሙሉ መውጣት የሚጀምሩት ብዙም ሳይቆዩ አይመስላችሁም?
ምክንያቱም ራሽያ መሰረታዊ የሚባለውን የአውሮፓ የገበያ ድርሻ በተለይ ነዳጅ፤ ማዳበሪያ፤ ብረት፤ ስንዴ፤ ወዘተ ላይ ተፅኖ አላት (ምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ከከፍተኛው 100% እስከ ዝቅተኛው 20% ድርሻቸው ከራሽያ ነው)።
ስለዚህ በስሜት የሚያዘንቡት ማዕቀብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪም ኢኮኖሚያቸው ላይ የአቅርቦት እና የፍላጎት ክፍተት መፍጠሩን ከአሁኑ እየተመለከቱ ነው።
ስለዚህ ሊያበቃለት ለሚችል የሶስተኛ ወገን ችግር ኢኮኖሚያቸው እንዲናጋ ለመፍቀድ ቅድሚያ ትንንሾቹ ሀገራት በመቀጠል ትልልቆቹ በጥልቀት ላይደፍሩ ይችላሉ።
#ለምሳሌ፦ የራሽያ ባንኮችን ከስዊፍት ማገድ የገንዘብ ዝውውሮችን እና ኢንቨስትመንትን ሊጎዳ መቻሉን በመረዳት በአንዴ የተስማሙበት ማዕቀብ መሆን አይችልም (#ለምሳሌ፦ ጀርመን የዚህ አይነቱ ማዕቀብ እዳው ለጀርመንም መሆኑን በመረዳት ክርክር ላይ ነች)።
ጦርነቱ ከፍቶ እና በሀይል ሚዛንነት ራሽያ ዩክሬንን ብታፈርሳት በዩክሬን ትከሻ የነበሩ ስንዴ፤ ብረት፤ የምግብ ዘይት፤ በቆሎ፤ ወዘተ በመሰረታዊነት የቀጠናው አምራች ሆና የምትቆየው ራሽያ ስለምትሆን ይህን ሁሉ ማጣት ቀላል ሊሆን አይችልም።
ትናንት ሙሉ አውሮፓን በካርታ ላይ ያላቸውን ቅርበት፤ የየብስ (የቱቦ መስመርን ጨምሮ) እና የባህር የንግድ ቅርበት፤ የንግድ Trend እና ጥልፍልፎሽ ስመለከት የመጣልኝ ሃሳብ ይህ ነው።
#ለምሳሌ፦ በዚህ ወቅት ቻይና የስንዴ ምርት ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ክልከላዋን ለማንሳት እቅድ አላት! ስለዚህ የዓለም ገበያ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ብቻ ያለው ባለመሆኑ ቻይና ለነማን ቅድሚያ ትሰጣለች? የሚለው ሃሳብም/ስጋትም አይጠፋም።
#ለምሳሌ፦ ኮቪድ በተቀሰቀሰ ወቅት ድንበር መዝጋት እና ድጎማ ማቅረብ አብዛኛው በጋራ የመሰደው እርምጃ ቢመስልም ኢኮኖሚያዊ ጫናውን በመፍራት ስትራቴጂካል ሽፍት ሲደረግ የታዘብነው ይህንን ነበር።
ማዕቀብ ዩክሬንን ለማዳን ሳይሆን በረጅም ጊዜ ራሽያን ለማዳከም ነው የሚያገለግለው። ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች እያሉ ጦርነቱ የመቆሞ አዝማሚያ የማያሳየው በዚህ Assumption ነው።
ኢራን፤ ቻይና፤ ሶሪያ፤ ቱርክ፤ ኢራቅ፤ አፍጋሃኒስታን ካላቸው የምዕራቡ ጥላቻ እና አሁንም በማዕቀብ ውስጥ በመሆናቸው ከራሽያ እየተገበያዩ ሊቆዩ ይችላሉ። ይህ ምን አልባት ለራሽያ ከአውሮፓ የጠፋውን የገበያ ድርሻ መቀበያ ሆኖ ሊያገለግላት ይችላል (ወደፊት ራሽያ ማዕቀቡን ለመቋቋም እያቀደች የሚሆነው እንዲህ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ኢራን ከ2018ቱ የአሜሪካን ማዕቀብ ጀምሮ ይህንን ስልት ስትጠቀም ነበር)።
ራሽያ ዩክሬን በመዝመቴ የማጣው፡Opportunity Cost of ዩክሬንን መውረር #ማዕቀብ መሆኑ መቼም አይጠፋትም! ነገር ግን በውጪ ንግድ ወሳኝ ተዋናይ በመሆኗ ነገሮችን ለመቋቋም እንደሚያግዛት ሳትደምር ሳትቀንስ የቆየች አይመስለኝም።
በቀጣይ መሰረታዊው ጥያቄ የትኛው ሀገር ነው ማዕቀብ ከተጣለባት ራሽያ ለመገበያየት የሚደፍረው የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው። ለምን? ምክንያቱም ማዕቀብ ከተጣለባት ሀገር መገበያየት በምዕራቢያኑ የተናጥል እና የተቋማት ማዕቀብ/ጫና ስለሚያስከትል ነው።
#ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ ነዳጅ ከሳውዲ ትገዛለች። በተመሳሳይ ስንዴ ከራሽያ ትሸምታለች። ስለዚህ ሳውዲ ራሽያ ላይ ማዕቀብ ብትጥል በቀጣይ ሳውዲ ኢትዮጵያ ከራሽያም ወዳጅ ሆና በነዳጅ ገበያውም ከሷ እንድትቀጥል በቀላሉ የምትቀበለው ይሆናል? በዓመት 3 ቢሊየን ዶላር ብቻ ሸመታ ላለው የኢትዮጵያ ፍላጎት ሳውዲ አማራጭ ታጣለች?
አሁን ጦርነቱን መደገፍ እና አለመደገፍ ማለት በቀጣይ ጊዚያት የገበያ አጋርን ማጣት እና አለማጣት ማለትም ነው። ስለዚህ በሳል ሆኖ መቆም ጥሩ ነው (የሰሞኑ የኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ አካሄድ የአራዳ ነው)።
#ለምሳሌ፦ አሜሪካ HR6600 የማዕቀብ እቅድ በኢትዮጵያ ላይ አላት ይህ ሰነድ ከፀደቀ መከራ ነው! ነገር ግን በቀጣይ እንዳይፀድቅ ራሽያን አውግዢ እና መግላጫ አውጪ የሚል ምርጫ ለኢትዮጵያ ቢሰጥ መልሱ ምንድን ይሆናል? (ራሽያ ገደል ትግባ ቪቫ አሜሪካ! ወይስ ማዕቀቡ ይምጣ ተስፋዬ ከራሽያ እጅ አለ ነው!)።
ድምፅ የነፈጉ የአፍሪካ ሀገራት በቀጣይ ቀናት የቀጥታም የተዘዋዋሪም የምዕራባውያንን ልመና እና ዛቻ እንዴት ያስተናግዱት ይሆን!?
Comments
Post a Comment