💚ይቅር ባይ ሁን

💛 ዓለም በአዎንታዊና አሉታዊ ነገሮች የተሞላች ናት፡፡ ከአንድ መልካም ነገር ጎን ሌላ መጥፎ ነገር አለ፡፡ በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥም ሌላ መልካም ነገር ይገኛል፡፡

❤️ከዚህም የተነሣ በሌሎች ሰዎች መገፋታችን ወይም እኛ ሰዎችን መግፋታችን አይቀርም፡፡ ይህ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕይወታችን ከሌሎች ጋር የተቋጠረና የተነካካ ነው፡፡ እኛነታችን ሌሎችን ይፈልጋል፡፡ እኛም ለሌሎች እናስፈልጋለን ፡፡ ሁሉም ሰው ከሌሎች የሚቀበለው ነገር አለው፡፡ ለሌሎች ሰጪም ነው፡፡

💜 መሳሳት የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ዳሩ ግን መሳሳት የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም፡፡ ስህተት የእንቅስቃሴና የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ሰለዚህም መሳሳት በየትኛውም የሕይወት ገጽ ላይ ሊከሰት የሚችለው ፡፡

❤️ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ መሳሳትና ማጥፋት አስቀያሚ ድክመት ነው፡፡ ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ ፡፡ ከተገፋንም በይቅርታ እንለፍ፡፡ ይህ የአእምሮ ብስለትና የመንፈስ ጥንካሬ ማሳያ ነው፡፡

️❤️💛💜❤️💛💜❤️💛💜


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች