ወረርሽኞችን እንዴት ማስቆም ይቻላል
*************************************
አለማችን በልዩ ልዩ ወረርሽኞች ተጠቅታለች፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ተስፋችንን በክትባቶች ላይ ብንጥልም እውነቱ ግን አብዘኞቹ ወረርሽኞች እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁ መሆኑ ነው፡፡ የጥንት ሰዎች ልክ እንዳሁኑ በተለያዩ ወረርሽኞች ተጠቅተዋል፡፡
ለምሳሌ The Black Death እየተባለ የሚጠራው ከ1346-1353 የተከሰተው ከሁሉም በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተከሰተው በልዩ ልዩ ጥናቶች እንደተመለከተው ለ2000 ዓመታት ያክል ወረርሽኝ ሆኖ የተከሰተው ምንጩ ባክቴሪያ የሆነው yersinia pestis ሌላው በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የወረርሽኞች የመስፋፋትና የገዳይነት አቅምም እየጨመረ መምጣቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
የሆንግ ኮንግ ጉንፋን እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ቢሆንም አሁንም ግን ስርጭቱ አላቆመም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት አስርት አመታት በፊት የተከሰተው ኤች አይ ቪ ቫይረስ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ስርጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እንደ WHO የቁጥር መረጃ ከሆነ በ2019 ብቻ በአለም ዙሪያ 690 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ሌላም ሳርስ የተባለ ከ2002-2003 ብቻ 800 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን የቀጠፈ በሽታ በአለማችን መከሰቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ የሞት መጠኑ ያልታዎቀ በግማሽ አመት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ኮቪድ 19 ተከሰተ፡፡
በአጠቃላይ በአለማችን የተከሰቱ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ስንመለከት በቁጥጥር ስር ለመዋል ረጅም አመታትና ብዙ ትውልዶች ስፈልጓቸዋል፡፡ በመሆኑም ስለ ወረርሽኞች ያለን እውቀት መዳበር፣ የማህበረሰብ አጠቃላይ ጤና መሻሻል፣ አዳዲስ ክትባቶች መገኘታቸው የየራሳቸው የሆነ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚያግዝ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት ዘርፈ ብዙ ጥናቶች የተደረጉ ቢሆንም እንዲሁም ስልጣኔ እየጨመረ ሲሄድ የክትባት ፍለጋው እየተሳካ ቢመጣም የውሸባን (ቀሳ) (quarantine) ያክል ግን ውጤታማ የሆነ መፍትሔ አልተገኘም፡፡ አሁን እያለፍንበት ያለውም ወረርሽኝ ማብቂያ ሊገኝ የሚችለው ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሔዎች በጥምረት በተግባር ሲውሉ ብቻ ነው፡፡
ምንጭ BBC news
Comments
Post a Comment