የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም!
====================
(ሥነ-ልቦናዊ መፍትሔ)
“በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቺያለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፊያለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቂያለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - ማይክል ጆርዳን።
አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡
የዚህ አመለካከት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ሥነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡
የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡
1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው፣
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡
2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው፣
ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡
3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው፣
ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡
___
ምንጭ:- "የአሸናፊነት ስነ-ልቦና" የፌስቡክ ገጽ፤
Popular posts from this blog
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች.....#share *ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ ነቢይ በሀገሩ አይከበርም። *መዐር አይጥዕሞ ለአድግ ለአህያ ማር አይጥማትም *አድኅን ርእስከ ራስህን አድን *አፍ ይጼውአ ለሞት አፍ ሞትን ይጠራል *ለሰሚዕ እጽብ ለሰሚው አስደናቂ *ብላዕ በሐፈ ገጽከ ጥረህ ግረህ ብላ *አክብር አባከ ወእመከ አባትና እናትህን አክብር *ተፋቀሩ በበይናቲከሙ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ *ኀላፊ ንብረት፣ክመ ጽላሎት ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው *እምነ ረሃብ የኄይስ ኩይናት ከረሀብ ጦርነት ይሻላል። *ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል ለሚያምን ሁሉ ይቻላል *ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ ያይን በሽታዋ ጠላትን ማየቷ *እለ ከርሦሙ አምላኮሙ ሆድ አምላኪዎች *ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለከ ለለመነህ ሁሉ ስጥ *በቁስለ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን *አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ ለሮጠ አይደለም ለቀደመ እንጅ *አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ *እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት። *ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ *መኑ ከመ አምላከነ? እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ? *አኮ በሲበት አላ በአእምሮ በሽበት አይደለም፤በማስተዋል እንጅ *ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ *ሀቡ ዘነጋሢ ለነጋሢ፤ወዘተረፈእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር፤የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ። ...
❤️ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች ራስህን አታስጨንቅ። ❤️የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ? ብታመዛዝነው የቱስ ይበልጣል? መለወጥ የምትችላቸውን ዛሬ ጀምር። መለወጥ የማትችላቸውን ነገሮችን ግን ተቀበላቸው። ❤️አንዳንዴ ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው አታስመስል! ሌሎችን ለምምሰል በመጣር ራስህን አትጣ። ❤️ራስህን መሆን ነፃ ያድርጋል ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር። ራስህንም ከፍ ከፍ አድርገው እችላለሁ አደርገዋለሁ በል አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም!! በምትችለው ሰዎችን እርዳ,,,አመስጋኝ ሁን መልካም ሰዎችን አመስግናቸው። ሁሌም አዲስ ቀን ሲሰጥህ ፈጣሪህንም ማመስግን አትርሳ።
Comments
Post a Comment