Posts

Showing posts from October, 2020
Image
 የናኖ ቴክኖሎጂ *********** ይህ አስገራሚ ዘርፍ የኢንጅነሪንግ፣ የሳንስና ቴክኖሎጂ ጥምረት ሲሆን መጣም ጥቃቅን ስለሆኑ ነገሮችም የሚያጠና ነው፡፡ ከ1-100 ናኖሜትር የሚደርስ መጠን ያላቸውን ትኩረት ያደርጋል፡፡ የዚህ ቴክኖሎጂ አባት እየተባለ የሚጠራው Richard Feynman ነው፡፡ የዚህ ሀሳብ ጥንስስ የተጀመረው በታህሳስ ወር 1959 የአሜሪካ የፊዚክስ ምሁራን ውይይት ጊዜ Richard Feynman ባነሳው “There’s Plenty of Room at the Bottom” በሚል ሀሳብ ነው፡፡ በውይቱ ፌይንማን እያንዳንዱን ሞሎኪዩልና አቶም እንዴት ነጣጥሎ ማጥናት እንደሚቻል አስረድቷል፡፡ ናኖ ቴክኖሎጂ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለማሰብ እጅግ በጣም ይከብዳል፡፡ አንድ ናኖ ሜትር አንድ ቢሊዮንኛ ሜትር ነው፡፡ በአንድ ኢንች ውስጥ 25,400,000 ያክል ናኖ ሜትሮች አሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ የጋዜጣ ወረቀት 100,000 ናኖ ምትር ውፍረት አለው፡፡ ተመራማሪዎች STM (scanning tunneling microscope) እና AFM (atomic force microscope) የሚባሉ ማይክሮስኮፖችን ከፈጠሩ በኋላ የናኖ ስኬል በሰፊው ስራ ላይ መዋል ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ይህ ቴክኖሎጂ በተለዩ መስኮች ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የፀሐይ መከላከያ ሎሽኖች (sunscreens) የተለያዩ የአይን መነጽሮች (Self-cleaning glass) አልባሳት እና ጸረ-ባክቴሪያ መጠቅለያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ምንጭ፡ National Nanotechnology Initiative  
 ✍️ ሰው እንደተወለደ የሚያለቅሰው ለምንድንነው?  አለኝ አንድ ወዳጄ :-  እኔሞ እንዲህ ስል መለስኩለት :: መወለድ ወደ ስቃይ መከራና ሰቆቃ መምጣት ነው:: መወለድ ስቃይን ማለፍ ነው መከራን መጋፈጥ ነው ሰቆቃን ታግሎ ድል መንሳት ነው::መወለድ ከአለመኖር ወደ መኖር መምጣት ነው:: መኖር ደግሞ ለህይወት ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ነው:: ለፈቃደ ስጋዊ ተግባር ሁሉ ተጠያቂ መሆን ነው:: ህይወት ጣዕም እንዲኖራት ጥሩ መዓዛ ያለውን የነፍስ የስጋና የፈቃድ ኡሁደት መፍጠር ነው::ይህን ማድረግ ደግሞ ብዙ ዳገት መውጣትንና ብዙ ቁልቁለት መውረድን የሚጠይቅ ነው:: ለዚህ ነው ወደምድር ስንመጣ የምናለቅሰው .....የወደፊቱን ስቃይ ፈተናና ወሰን የሌለውን በፍላጎት እሳት የምንቃጠለውን አመልካች ነው::        ቸር ሁኑ!!
 ✍️ ትክክለኛው መንገድ ላይ ሳትሆን መሮጥ ትርጉሙ ምንድን ነው? ሕይወት የእሽቅድድም መድረክ ነው:: በየፊናው ውድድር እና ጥሎ ማለፍ የሞላበት ክስተት ነው:: በትክክለኛው የህይወት ጎዳና ላይ ሳንሆን የምናደረገው እሽቅድድም ግን የማይረባና ትርጉም የሌለው ነው:: ውጤቱም ውድቀት ነው:: ምንም ያክል ረጅም ርቀት ቢኬድም መንገዱ ትክክለኛ ካልሆነ የተሻለ መፍትሄዉ መሮጥ ሳይሆን ወደኋላ መመለስ ነው:: መነሻዉ መድረሻውን የሚወሰነው የህይወት ሩጫ አለ:: ጅማሪው ትክክለኛው ካልሆነ ፍፃሜውም ስህተት ነው:: ለዚህ ደግሞ የተሻለ አማራጭ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን ሳናረጋግጥ አለመሮጥ ነው:: የትኛውንም ተግባራዊ እርምጃ ከማድረግ በፊት ማሰብ ማሰላሰል እና መመርመር ያስፈልጋል:: ጥልቅ በሆነ ማሰብና ማሰላሰል ውስጥ ህልውና ንቁ ይሆንና የሚደረገው ተግባራዊ እርምጃ ትክክል መሆን አለመሆኑን ያሳውቃል :: ይህን ሂደት አልፎ የሚከወን ተግባርም ሙሉ በሙሉ ከስህተት ባይፀዳም ትርጉም ያለው ይሆናል ::       ***ብሩህ ጊዜ🙏🙏🙏
 ✍️ በንፅህና መለኮት አንዴ ከተዋሃዳችሁ በህያውነት ዘለቀት ውስጥ ያለማቋረጥ እየጣፈጣችሁ ነው ማለት ነው:: ልክ ቡና ወተት ጋር ሲዋሃድ ማኪያቶ እንደሚሆነው....ከተዋሃደ በኋላ ወተቱን ከማኪያቶ መለየት እንደማይቻል ሁሉ ከፈጣሪ ንፅህና (ፍቅር:-እውነት) ጋር ስትዋሃዱ የህያውነት አካል ሆናችሁ ማለት ነውና ለፈጣሪ ልባችሁን በንፅህና ካሰናዳችሁ ፍቅር ተከስቶአል ሲከሰት ደግሞ ላይለያችሁ ተዋህዷል       🙏ንቃት🙏
 ✍️ ህይወት በየ ቅፅበት የምትገለጥ እንደ ጠብታ መጥፋትም መስፋትም የምትችል አዲስ ምዕራፍ ናት:: ትላንትን ኑረን አልፈናል ዛሬ ደግሞ ይህው ቀርቦልናል ህይወታችን በትላንት ስላልተወሰነ ዛሬ በአዲስ መልክ ቀርቧል::    ትዝታ ደግሞ ህይወትን ወደኋላ ለመጎትት የሚኮትን ሀይል ሁኖ ተደቅኗል :: በዚህ ሀይል ሳንታሰር ዛሬን በአግባብ እየኖርን ነገን የተሻለ እንዲሆን የምናልም ብቁ ሰው እንሁን!!
Image
 ምድርን ከአደጋ መጠበቅ ይፈልጋሉ ********************************** የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ያለንበትን የአየር ጠባይ ለውጥ እንደዋዛ መመልከት እንደማገባ በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡ የአየር ጠባይ ለውጡ በአለማችን ታይተው የማይታወቁ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ከማስከተሉም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ምርት ማነስን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የውሀ አካላት ከልካቸው በማለፍ በየአካባቢው የጎርፍ አደጋን እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ሀገራት ይህ የተፈጥሮ መናጋት ወደማይመለስበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት አስቸኳይ እርምጃን መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ መንግስታት መስራት ያለባቸውን እስኪሰሩ ድረስ እያንዳንዱ ሰው በግለሰብ ደረጃ የሚኖርባትን ምድር መንከባከብ የሚችልበትን መንገድ ከዚህ እንደሚከተለው ልናስነብባችሁ ወደድን፡፡ መልካም ንባብ 1ኛ. ውሃን በአግባቡ መጠቀም ስናያቸው ትንሽ ናቸው ብለን የምናስባቸው ነገሮች በትኩረት መሰራት ከቻሉ ትልቅ ለውጥ ማምታት ይችላሉ፡፡ በማንናውም ሰዓት ለምሳሌ ምሳ ለመብላት እጅ ስንታጠብ ወዲያው የመታጠቢያውን ውሀ መዝጋት ከቻልን እና ሌሎችም ይህን እንዲያደርጉ ከገፋፋን በቀላሉ የውሀ ብክነትን መቀነስ እንችላለን፡፡ በእርግጥ ውሃ የሚባክንበት ምክንያት ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን አንድን ነገር ለመስራት የሚያስፈልገንን ውሃ ብቻ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በተቻለ መጠን ውሀን ከቤታችን እያጣራን እንጠቀም፡፡ በዚህ ምክንያት ምድራችንን ከፕላስቲክ ኮዳዎች መታደግ እንችላለን፡፡ 2ኛ. መኪና የመጠቀም ልምዳችንን እንቀንስ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መኪና ይዞ መውጣት ጊዜያዊ የጤና ችግር ከማስከተሉ በተጨማሪ የካርቦን ልቀትን በማስፋፋት የተፈጥሮን ሚዛን ያዛባል፡፡ ከተቻለ ለ2 ቀን ከመኪና መንገድ ራቁ፡፡ መኪና መጠቀም ...
Image
 ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ይሕ Ethio Job Vacancy ነው። የወጣበት ቀን መስከረም 27/2013 ዓ.ም ምንጭ:- ሪፖርተር ጋዜጣ በሪፖርተር ጋዜጣ የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን ለማግኘት https://www.ethiopianreporterjobs.com ይጎብኙ መረጃውን #like  #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም ያካፍሉ። ሌሎችን የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ በሙሉ Please Join here.. www.facebook.com/groups/ethiojobvacancy/ Click here Blogger site https://oneethiopia1.blogspot.com/
Image
 የአፍንጫ መድማትን ለማቆም የሚያስችል መንገድ ******************************** ምንም እንኳን የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር አስደንጋጭ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የተለመደ ነው፡፡ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የአፍንጫ መድማት ይታይባቸዋል፡፡ በተለይ ከ2-10 ዕድሜ ክልል ያሉ ህፃናትና ከ50-80 ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ከፍተኛውን የቁጥር ድርሻ ይወስዳሉ፡፡    አፍንጫችን የምንስበውን አየር የሚያረጥቡ ብዙ የደም ስሮች አሉት፡፡ በአፍንጫችን በኩል የሚገባው አየርም ወደ አፍንጫችን ግድግዳ ተጠግቶ በሚያልፍበት ወቅት ለዚህ የመድማት ችግር ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው ከፍተኛ ግፊት ያለው ነፋስ ሲኖርና በእጃች አላስፈላጊ መነካካት ስናዘወትር ነው፡፡ እዚህ አካባቢ የሚከሰት መድማት anterior nosebleeds በመባል ይታወቃል፡፡ ብዙ ጊዜ ያልተለመደውና የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለው ከውስጠኛው የአፍንጫ ስር የሚመነጨው posterior nosebleeds የሚባለው ነው፡፡ ልዩ ህክምናም የሚስፈልገው የአፍንጫ መድማትም ይህኛው ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የአፍንጫ መድማት በአደጋ የአፍንጫ መሰበር ሲያጋጥም፣ የቅርብ ጊዜ የአፍንጫ ቀዶ ህክምና ሲኖር፣ ደምን ሊያቀጥኑ የሚችሉ መድሀኒቶችን ስንጠቀም፣ የደም ስሮችን የሚጎዳ ተፈጥሯዊ ችግር ሲኖርና የሉኪሚያ ተጠቂ ስንሆን የሚከሰት ነው፡፡ ይሁንና የአፍንጫ መድማትን በቀላሉ በቤት ውስጥ ማሰቆም ይቻላል፡፡ ችግሩን ለማስቆም ብዙ መንገዶች ቢኖሩም በአሜሪካ የሚገኘው Yale Medicine ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተሎች መከተል ተገቢ ነው ይላል፡፡   ተስተካክሎ በመቀመጥ የአፍንጫን ለስላሳውን ክፍል በለስላሳ ጨርቅ ወይም በሶፍት ለ10 ደቂቃ...
Image
 Never forget the hands that raised you !! ያሳደጉህን እጆች በጭራሽ አትርሳ !!  
Image
 💚ይቅር ባይ ሁን 💛 ዓለም በአዎንታዊና አሉታዊ ነገሮች የተሞላች ናት፡፡ ከአንድ መልካም ነገር ጎን ሌላ መጥፎ ነገር አለ፡፡ በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥም ሌላ መልካም ነገር ይገኛል፡፡ ❤️ከዚህም የተነሣ በሌሎች ሰዎች መገፋታችን ወይም እኛ ሰዎችን መግፋታችን አይቀርም፡፡ ይህ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕይወታችን ከሌሎች ጋር የተቋጠረና የተነካካ ነው፡፡ እኛነታችን ሌሎችን ይፈልጋል፡፡ እኛም ለሌሎች እናስፈልጋለን ፡፡ ሁሉም ሰው ከሌሎች የሚቀበለው ነገር አለው፡፡ ለሌሎች ሰጪም ነው፡፡ 💜 መሳሳት የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ዳሩ ግን መሳሳት የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም፡፡ ስህተት የእንቅስቃሴና የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ሰለዚህም መሳሳት በየትኛውም የሕይወት ገጽ ላይ ሊከሰት የሚችለው ፡፡ ❤️ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ መሳሳትና ማጥፋት አስቀያሚ ድክመት ነው፡፡ ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ ፡፡ ከተገፋንም በይቅርታ እንለፍ፡፡ ይህ የአእምሮ ብስለትና የመንፈስ ጥንካሬ ማሳያ ነው፡፡ ️❤️💛💜❤️💛💜❤️💛💜  
 የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም! ==================== (ሥነ-ልቦናዊ መፍትሔ) “በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቺያለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፊያለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቂያለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - ማይክል ጆርዳን። አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡ የዚህ አመለካከት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ሥነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡ የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት ...
Image
 ወረርሽኞችን እንዴት ማስቆም ይቻላል ************************************* አለማችን በልዩ ልዩ ወረርሽኞች ተጠቅታለች፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ተስፋችንን  በክትባቶች ላይ ብንጥልም እውነቱ ግን አብዘኞቹ ወረርሽኞች እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁ መሆኑ ነው፡፡ የጥንት ሰዎች ልክ እንዳሁኑ በተለያዩ ወረርሽኞች ተጠቅተዋል፡፡ ለምሳሌ The Black Death እየተባለ የሚጠራው ከ1346-1353 የተከሰተው ከሁሉም በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተከሰተው በልዩ ልዩ ጥናቶች እንደተመለከተው ለ2000 ዓመታት ያክል ወረርሽኝ ሆኖ የተከሰተው ምንጩ ባክቴሪያ የሆነው yersinia pestis ሌላው በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የወረርሽኞች የመስፋፋትና የገዳይነት አቅምም እየጨመረ መምጣቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ የሆንግ ኮንግ ጉንፋን እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ቢሆንም አሁንም ግን ስርጭቱ አላቆመም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት አስርት አመታት በፊት የተከሰተው ኤች አይ ቪ ቫይረስ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ስርጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እንደ WHO የቁጥር መረጃ ከሆነ በ2019 ብቻ በአለም ዙሪያ 690 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይዎታቸው አልፏል፡፡ ሌላም ሳርስ የተባለ ከ2002-2003 ብቻ 800 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን የቀጠፈ በሽታ በአለማችን መከሰቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ የሞት መጠኑ ያልታዎቀ በግማሽ አመት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ኮቪድ 19 ተከሰተ፡፡ በአጠቃላይ በአለማችን የተከሰቱ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ስንመለከት በቁጥጥር ስር ለመዋል ረጅም አመታትና ብዙ ትውልዶች ስፈልጓቸዋ...
Image
 የእይታ ችግር ላለባቸው ትልቅ መላ ********************************** ቺይኮ አሳካዋ ትባላለች፡፡ አይነ ስውር ናት፡፡ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ስትሆን በስራ ምክንያት በየወሩ ከአሜሪካ ጃፓን ከጃፓን አሜሪካ የአውሮፕላን ጉዞ ታደርጋለች፡፡ በረራ ያደረገችው ብቻዋን ከሆነ ከአየር መንገዱ ሰራተኞች አንዱ ወደምትፈልገው ቦታ ያደርሳታል፡፡ ካልሆነም የምትፈልገውን ሰው እስክታገኝ ለረጅም ሰዓት ትጠብቃለች፡፡ ችግር ብልሀትን ይወልዳል እንዲባል በዚህ ነገር የተማረረችው ቺይኮ ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሻንጣን ሰርታ አቅርባለች፡፡ ይህም ፈጠራዋ ከአውሮፕላን ከወረደች በኋላ በፍጥነትና ደህንነቷ እንደተጠበቀ ወደ መዳረሻዋ የሚመራት ነው፡፡ ሻንጣው የጉዞ ሻንጣ ሲሆን ካሜራና ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ ካሜራና ሴንሰሩ በአብዛኞቹ ራስ ነድ መኪኖች (autonomous car) እንደተገጠሙት ያለ ነው፡፡ ሻንጠው አካባቢውን እንዲያውቅ ሰው ሰራሽ ክህሎትን (artificial intelligence) ይጠቀማል፡፡ ሻንጣውን ለማዘዝ የሞባይል መተግበሪያ እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሻንጣው የሰው ፊት መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል፡፡ ይህም ተጠቃሚውንና በቅርብ ያለ ሰውን እንዲለይ ያስችለዋል፡፡ ይህች ድንቅ እንስት ሌሎች ብዙ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለአለም ያስተዋወቀች ሲሆን ከእነዚህም መካከል   "aDesigner," ለዲዛይነሮች የሚያግዝና ዌብሳቶችን ለተጠቃሚዎች ቀላል የሚያደርግ ቴክኖሎጂ፣ በድምጽ ኢንተርኔት መክፈት የሚያስችል በተለይ ለአይነ ስውራን ምቹ የሆነ ፈጠራ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ባለድንቅ ቴክኖሎጂውን ሻንጣ ለመስራት ያነሳሳትን ነገር ስትናገር " ብቻየን ስራመድ ምንም ምቾት አይሰማኝም፡፡ ሁልጊዜ በጉዞ ብቸኝነቴን ሊቀርፍል...
Image
 የደም እንባ መስከረም 25 ቀን 2013ዓ.ም የ15 አመቷ ብራዚላዊት ልጃገረድ ሀኪሞች ሊደርሱበት ባልቻሉበት ሁኔታ ከሳምንት ለበለጠ ጊዜ ከአይኖቿ ደም መፍሰስ እንደጀመረ ኦዲቴ ሴንትራል በሰሞኑ የዜና ገጹ አስነብቧል:: ዶሪስ እ.ኤ.አ መስከረም 12/2020 በመታመሟ ምክንያት እናቷ ሳኦፖሎ ወደ ሚገኘው ሆስፒታል ስትወስዳት የኩላሊት ጠጠር ተብላ መድሃኒት ሰጥተዋት ወደ ቤቷ ተመልሳ ነበር ::በነጋታው ግን ከአንድ አይኗ ደም መፍሰስ በመጀመሩ ድጋሚ ወደ ሆስፒታል ታመራለች፤ ይህን ተከትሎም ዶክተሮች የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያካሂዱላትም በምን ምክንያት ከአይኗ ደም ሊፈስ እንደቻለ ማወቅ አልቻሉም::  ምንም አይነት ህመም ስለማይሰማትም ወደ ቤት እንድትሄድ ቢያደርጓትም ከእንደገና ሁለቱ አይኖቿ ድጋሚ ደም ማፍሰስ በመጀመራቸው አሁንም ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች:: ይሁንና ዶሪስ ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ ማወቅ አልተቻለም:: የአይን ሃኪም የሆኑት ራፋኤል አንቶኒዮ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር በህክምና  ቋንቋ  ሄሞላክሪያ ተብሎ ይጠራል:: ህክምናውም እንደተነሳበት ምክንያት ይሰጣል:: አንዳንዴም በራሱ ጊዜ የሚጠፋ በመሆኑ መድሃኒት አያስፈልገውም::  ዶ/ር ሊአንድሮ ፎንሲካ እንደገለጹት ደግሞ ይህ ሁኔታ በህመምተኛው ሰውነት ውስጥ በሚፈጠር ችግር የሚከሰት ሲሆን ለማከምም ያን ያህል ውስብስብ አይደለም:: በጸረ ተህዋሲያንና በሆርሞን ህክምና ይታከማል:: አልፎ አልፎ ግን ሁኔታው ለሌላ የጤና እክል ታማሚውን ሊዳርግ ይችላል::  
Image
 To enjoy the beauty of life, live in the moment, not in the future.
  ለዜና አንባቢውና አቀንቃኙ ተወዳጁ ድምጻዊ Yidinekachew ዜማና ግጥም ሊሰጠው ነው    
Image
 All great achievements require time.  ሁሉም ታላላቅ ስኬቶች ጊዜ ይፈልጋሉ፡፡
Image
 Don't wait for the opportunity, create it.  ዕድሉን አይጠብቁ፣ ይፍጠሩ፡፡
Image
 ውጥረት በየዕለቱ የሚያጋጥመን ክስተት ነው። በብዙ ነገሮች ምክንያት ውጥረት ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ምንጫቸውም ብዙ ነው። አንዳንዶቹንም ራሳችን እንፈጥራቸዋለን። አንዳንዶቹ ደግሞ በአካባቢያችን  ምክንያት ይፈጠራሉ። ዋናው ነገር እነዚህን መቋቋም የተለያዩ መንገዶችን መጠቀም ነው። መንገዶቹም እንደየውጥረት አይነቶቹ የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ከውጥረት ነጻ የሆነ ቀን ተመኘን!  
Image
  ❤️ብዙዎቻችን የቤት ውስጥ ሂደት ውስጥ በኅብረተሰብ ውስጥ እንዴት ጠባይ ማሳየት እንደምንችል የሰለጠንን ሲሆን ይህም የዓለምን ባህርይ የምንቀርፅበት የሽልማትና የቅጣት ሥርዓት ነው ፡፡ በዚህ የሽልማትና የቅጣት ስርዓት አማካይነት እኛ የምንጠብቀውን ካልጠበቅን እንቀጣለን እናም እያደግን ስንሄድ የውጭ ቅጣትን ለማስቀረት እራሳችንን መቅጣት የሚጀምር የውስጥ ዘዴ እንሰራለን - እና ቅጣት ብዙውን ጊዜ የሚመጣው በራስ የመቀበል ፣ በራስ የመጠራጠር ፣ በራስ የመፍረድ እና እንደ ሚያውቁት ብዙዎቻችን እራሳችንን ያለማቋረጥ በመገደብ እና በመፍረድ ነው ፡፡ 💜ለሌላ ሰው ተቀባይነት እና ተቀባይነት ለማግኘት እኛ ያልሆንነውን አንድ ነገር እንመስላለን ፡፡ እኛ በአንድ ተስማሚ ላይ በመመስረት የራስን ስሜት እንፈጥራለን ፣ እናም ያንን ተስማሚ ካልሆንን ፣ እፍረት ይሰማናል ፣ የጥፋተኝነት ስሜት እና ዋጋ ቢስ እንደሆነ ይሰማናል። ❤️ እኛ መሆን አለብን ብለን የምናስበውን ምስል - የፍጽምና ምስል ፣ ከማንኛውም እንከን ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነ ነገር እንፈጥራለን ፡፡ ይህንን የተሳሳተ የራስ-ምስል ሕያው ሆኖ እንዲኖር እና ቁጥጥር እንዲደረግበት ጊዜውን በሙሉ የሚሰጥ ውስጣዊ ተቺን በአዕምሯችን ውስጥ እናዳብራለን። 💛 መሆን አለብን ብለን ያሰብነውን ምስል ይጠብቃል ፣ ይወቅሰናል ፣ ይፈርዳል ፣ ያንን ምስል ባጣን ቁጥር ይቀጣናል ፡፡ እሱ ምን ሊያስፈራራው እንደሚችል ሁል ጊዜ ጠንቃቃ ነው ፣ ስለሆነም እኛ ከራሳችን ተስማሚ ምስል ጋር ላለመኖር በመፍራት ተፈጥሯዊ እና ድንገተኛ እንዳንሆን ያደርገናል። 💚እኛ ግን አብዛኞቻችን ይህንን ከማንነታችን እውነተኝነት ይልቅ የምናውቀው ስለሆንን እና ከውጭ ቅጣት እንደሚጠብቀን ስለሚሰማን እኛ ምንም እንኳን እራሳችንን የ...
 ሕዝቤማ ጀግና ነህ !      ትመግበው ማያይልቅ... ታጠጣው የማይደርቅ... ከደረቅ አፈር ስር፣ ሕይወት ምግብ ሠሪ፤ በተረሳ ቀየህ... ከተፈጥሮ ታግለህ፣ ትርፍ አምርቶ ኗሪ፤ ሀገር ክብር ነስታህ... ሀገር ገንብቶ ሟች፣ አልፎ አ ሻ ጋ ሪ። ከፍታህን የሚያክል፣ አንተን የሚመጥን፣ አጥተህ እንጂ መሪ፤ ሕዝቤማ ታላቅ ነህ... ትመስክር ይች ምድር፣ ይመስክር ፈጣሪ!!!
 "እኔ እዘጋዋለሁ፣ ቤቴን እንዳመሉ፤ የታ'ለ ቢሏችሁ፣ ከፍቶት ሄደ በሉ።" (የሕዝብ)
Image
  ውልደቱ ጎጃም ሲሆን ለቤተሰቡ አራተኛ ልጅ ነው ። ከውልደቱ ጎጃም ይልቅ ሐመሮች ማርከውታል። በሐመሮች መማረክ ብቻ ሳይሆን በብዕሩ ተከታታይ መጻሕፍት ደርሶላቸዋል። አስጊጦ ጽፎላቸዋል ። ፍቅረማርቆስ ደስታ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን በብሔረሰቦች ባህል ላይ ያተኮሩ ተከታታይ መፃህፍትን ያበረከተ ደራሲ ነው። 'ከቡስካ በስተጀርባ'፣ 'ኢቫንጋዲ'፣ 'የዘርሲዎች ፍቅር'፣ 'አቻሜ' ና 'የንሥር ዓይን' የተሰኙት በሐመር ብሔረሰብ ታሪክ ላይ ያተኮሩት መጻሕፍት የብሔረሰቡን ባህል ና ትውፊት ከማስተዋወቁም በላይ የህዝቡን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በድርሰቶቹ ያሳየን ደራሲ ነው ። ፍቅረማርቆስ የሐመር ብሔረሰብን ባህል የማስተዋወቅ ሥራውን አጠናክሮ በመቀጠል ለውጪው ዓለም አንባቢያን የሚሆን ሥራውን በእንግሊዝኛም አሳትሟል ። ይዀው ''Land of the Yellow Bull'' የተሰኘው መጽሐፉ በመላው ዓለም ተሰራጭቷል። 'የበጋው መብረቅ' በጃግማ ኬሎ የህይወት ታሪክ ላይ ያጠነጠነ መጽሐፍም ጽፏል ። በሀገራችን በመጽሐፍ ታሪክ ውስጥ ቁጥራቸው በከፍተኛ ሁኔታ ታትሞ ለሕዝብ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል የእሱ መጻሕፍት ተጠቃሽ ናቸው ። ከ''መቶ ሺህ'' በላይ መጻሕፍቱ ታትመው ለገበያ ቀርበው ተሽጦለታል ። አምስት መጻህፍቶቹ በገበያ ላይ ሲውሉ ከአንድ በላይ የመታተም ዕድልን አግኝተዋል ። የመጀመሪያ መጽሐፋ [ከቡስካ በስተጀርባ] ሰባት ጊዜ ታትሟል ፤ ሁለተኛው [ኢቫንጋዲ ] አምስት ጊዜ ፣ ሦስተኛው [የዘርሲዎች ፍቅር] አራት ጊዜ ፤ አራተኛው [አቻሜ ] ሁለት ጊዜ ፤ አምስተኛውም[ የንሥር ዓይን] እንዲሁ ሁለተኛ ጊዜ ታትሟል ። ስድስተኛው መጽሐፉን ለ...
Image
  ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ይሕ Ethio Job Vacancy ነው።   መስከረም   22 /2013 ዓ.ም (02 October 2020) G.C   Advert on Addis Zemen magazine (በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣ)   Gulele Botanic Garden 9 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው   መረጃውን #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም በስራ ፍለጋ ለሚንከራተቱ ወገኖቻችን እናካፍል።   ትክክለኛ የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ   Please Join here.. በቴሌግራም ቻናል... https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy                                          Blogger site Click here … https://oneethiopia1.blogspot.com/    
Image
  ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ይሕ Ethio Job Vacancy ነው።   መስከረም   22 /2013 ዓ.ም (02 October 2020) G.C   Advert on Addis Zemen magazine (በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣ)   Federal Procurement and Supply Administration Agency 2 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው   መረጃውን #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም በስራ ፍለጋ ለሚንከራተቱ ወገኖቻችን እናካፍል።   ትክክለኛ የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ   Please Join here.. በቴሌግራም ቻናል... https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy                                          Blogger site Click here … https://oneethiopia1.blogspot.com/      
Image
  ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ይሕ Ethio Job Vacancy ነው።   መስከረም   22 /2013 ዓ.ም (02 October 2020) G.C   Advert on Addis Zemen magazine (በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣ)   Gotera Masalecha Health Center   8 - ቦታዎች በ0አመት 18 - ቦታዎች ልምድ ላላቸው   መረጃውን #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም በስራ ፍለጋ ለሚንከራተቱ ወገኖቻችን እናካፍል።   ትክክለኛ የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ   Please Join here.. በቴሌግራም ቻናል... https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy                                          Blogger site Click here … https://oneethiopia1.blogspot.com/     
Image
  ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ይሕ Ethio Job Vacancy ነው።   መስከረም   22 /2013 ዓ.ም (02 October 2020) G.C   Advert on Addis Zemen magazine (በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣ)   Debera Tabor University 57 - ቦታዎች በ0አመት 1 - ቦታ ልምድ ላለው/ላላት   መረጃውን #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም በስራ ፍለጋ ለሚንከራተቱ ወገኖቻችን እናካፍል።   ትክክለኛ የሥራ ማስታወቂያ መረጃዎችን ለመከታተል ለምትፈልጉ በሙሉ Please Join here.. በቴሌግራም ቻናል... https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy                                          Blogger site Click here … https://oneethiopia1.blogspot.com/