ሕዝቤማ ጀግና ነህ !     

ትመግበው ማያይልቅ...
ታጠጣው የማይደርቅ...
ከደረቅ አፈር ስር፣ ሕይወት ምግብ ሠሪ፤
በተረሳ ቀየህ...
ከተፈጥሮ ታግለህ፣ ትርፍ አምርቶ ኗሪ፤
ሀገር ክብር ነስታህ...
ሀገር ገንብቶ ሟች፣ አልፎ አ ሻ ጋ ሪ።

ከፍታህን የሚያክል፣
አንተን የሚመጥን፣ አጥተህ እንጂ መሪ፤
ሕዝቤማ ታላቅ ነህ...
ትመስክር ይች ምድር፣ ይመስክር ፈጣሪ!!!

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች