የደም እንባ
መስከረም 25 ቀን 2013ዓ.ም

የ15 አመቷ ብራዚላዊት ልጃገረድ ሀኪሞች ሊደርሱበት ባልቻሉበት ሁኔታ ከሳምንት ለበለጠ ጊዜ ከአይኖቿ ደም መፍሰስ እንደጀመረ ኦዲቴ ሴንትራል በሰሞኑ የዜና ገጹ አስነብቧል::
ዶሪስ እ.ኤ.አ መስከረም 12/2020 በመታመሟ ምክንያት እናቷ ሳኦፖሎ ወደ ሚገኘው ሆስፒታል ስትወስዳት የኩላሊት ጠጠር ተብላ መድሃኒት ሰጥተዋት ወደ ቤቷ ተመልሳ ነበር ::በነጋታው ግን ከአንድ አይኗ ደም መፍሰስ በመጀመሩ ድጋሚ ወደ ሆስፒታል ታመራለች፤ ይህን ተከትሎም ዶክተሮች የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያካሂዱላትም በምን ምክንያት ከአይኗ ደም ሊፈስ እንደቻለ ማወቅ አልቻሉም::
 ምንም አይነት ህመም ስለማይሰማትም ወደ ቤት እንድትሄድ ቢያደርጓትም ከእንደገና ሁለቱ አይኖቿ ድጋሚ ደም ማፍሰስ በመጀመራቸው አሁንም ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች:: ይሁንና ዶሪስ ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ ማወቅ አልተቻለም::
የአይን ሃኪም የሆኑት ራፋኤል አንቶኒዮ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር በህክምና  ቋንቋ  ሄሞላክሪያ ተብሎ ይጠራል:: ህክምናውም እንደተነሳበት ምክንያት ይሰጣል:: አንዳንዴም በራሱ ጊዜ የሚጠፋ በመሆኑ መድሃኒት አያስፈልገውም::
 ዶ/ር ሊአንድሮ ፎንሲካ እንደገለጹት ደግሞ ይህ ሁኔታ በህመምተኛው ሰውነት ውስጥ በሚፈጠር ችግር የሚከሰት ሲሆን ለማከምም ያን ያህል ውስብስብ አይደለም:: በጸረ ተህዋሲያንና በሆርሞን ህክምና ይታከማል:: አልፎ አልፎ ግን ሁኔታው ለሌላ የጤና እክል ታማሚውን ሊዳርግ ይችላል::


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች