የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የሚያመጣው ኢኮኖሚያዊ ጫና
ራሽያን ማዕቀብ ውስጥ ማቆየት ማንን ይጎዳል? አውሮፓውያን በተናጥል ከራሽያ ማዕቀብ ማዕቀፍ ውስጥ በከፊል አልያም በሙሉ መውጣት የሚጀምሩት ብዙም ሳይቆዩ አይመስላችሁም? ምክንያቱም ራሽያ መሰረታዊ የሚባለውን የአውሮፓ የገበያ ድርሻ በተለይ ነዳጅ፤ ማዳበሪያ፤ ብረት፤ ስንዴ፤ ወዘተ ላይ ተፅኖ አላት (ምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ከከፍተኛው 100% እስከ ዝቅተኛው 20% ድርሻቸው ከራሽያ ነው)። ስለዚህ በስሜት የሚያዘንቡት ማዕቀብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪም ኢኮኖሚያቸው ላይ የአቅርቦት እና የፍላጎት ክፍተት መፍጠሩን ከአሁኑ እየተመለከቱ ነው። ስለዚህ ሊያበቃለት ለሚችል የሶስተኛ ወገን ችግር ኢኮኖሚያቸው እንዲናጋ ለመፍቀድ ቅድሚያ ትንንሾቹ ሀገራት በመቀጠል ትልልቆቹ በጥልቀት ላይደፍሩ ይችላሉ። #ለምሳሌ፦ የራሽያ ባንኮችን ከስዊፍት ማገድ የገንዘብ ዝውውሮችን እና ኢንቨስትመንትን ሊጎዳ መቻሉን በመረዳት በአንዴ የተስማሙበት ማዕቀብ መሆን አይችልም (#ለምሳሌ፦ ጀርመን የዚህ አይነቱ ማዕቀብ እዳው ለጀርመንም መሆኑን በመረዳት ክርክር ላይ ነች)። ጦርነቱ ከፍቶ እና በሀይል ሚዛንነት ራሽያ ዩክሬንን ብታፈርሳት በዩክሬን ትከሻ የነበሩ ስንዴ፤ ብረት፤ የምግብ ዘይት፤ በቆሎ፤ ወዘተ በመሰረታዊነት የቀጠናው አምራች ሆና የምትቆየው ራሽያ ስለምትሆን ይህን ሁሉ ማጣት ቀላል ሊሆን አይችልም። ትናንት ሙሉ አውሮፓን በካርታ ላይ ያላቸውን ቅርበት፤ የየብስ (የቱቦ መስመርን ጨምሮ) እና የባህር የንግድ ቅርበት፤ የንግድ Trend እና ጥልፍልፎሽ ስመለከት የመጣልኝ ሃሳብ ይህ ነው። #ለምሳሌ፦ በዚህ ወቅት ቻይና የስንዴ ምርት ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ክልከላዋን ለማንሳት እቅድ አላት! ስለዚህ የዓለም ገበያ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ብቻ ያለው ባለመሆኑ ቻይና ለነማን ቅድሚያ ትሰጣለች...