የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች.....#share
*ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ
ነቢይ በሀገሩ አይከበርም።
*መዐር አይጥዕሞ ለአድግ
ለአህያ ማር አይጥማትም
*አድኅን ርእስከ
ራስህን አድን
*አፍ ይጼውአ ለሞት
አፍ ሞትን ይጠራል
*ለሰሚዕ እጽብ
ለሰሚው አስደናቂ
*ብላዕ በሐፈ ገጽከ
ጥረህ ግረህ ብላ
*አክብር አባከ ወእመከ
አባትና እናትህን አክብር
*ተፋቀሩ በበይናቲከሙ
እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ
*ኀላፊ ንብረት፣ክመ ጽላሎት
ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው
*እምነ ረሃብ የኄይስ ኩይናት
ከረሀብ ጦርነት ይሻላል።
*ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል
ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
*ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ
ያይን በሽታዋ ጠላትን ማየቷ
*እለ ከርሦሙ አምላኮሙ
ሆድ አምላኪዎች
*ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለከ
ለለመነህ ሁሉ ስጥ
*በቁስለ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ
በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን
*አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ
ለሮጠ አይደለም ለቀደመ እንጅ
*አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ
ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ
*እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት
ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት።
*ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን
ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ
*መኑ ከመ አምላከነ?
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ?
*አኮ በሲበት አላ በአእምሮ
በሽበት አይደለም፤በማስተዋል እንጅ
*ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር
መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ
*ሀቡ ዘነጋሢ ለነጋሢ፤ወዘተረፈእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር
የቄሳርን ለቄሳር፤የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ።
*ሰለአሐዱ በከመ ምግባሩ
ሥራ ለሠሪው እሾህ ላጣሪው (ለእያንዳንዱ እንደሥራው)
*መኑ ዘደመሮ ለብርሃን ምስለ ጽልመት?
ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
*ማየ ብዙኅ ኢይክል አጥፍአታ ለፊቅር
ብዙ ውሃ ፍቅርን አያጠፋትም
*መጥወኒ እመጥወከ
ስጠኝ እሰጥሃለሁ (እከክልኝ ልከክልህ)
*ሰብእ ወጣኒ፣እግዚአብሔር ፈጻሚ
ሰው ይጀምራል፣እግዚአብሔር ይፈጽማል
*ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ እግዚአብሔር
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።
*ብእሲት አዛል (እዚዝ) እክሲል ለምታ
መልካም ሴትን ለባሏ ዘውድ ናት
*አልቦ ዘይእህዝ እርፈ ወየሐርስ ድኅሪተ
ዕርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም።
*አንፄዋ ለኅልፈታ አንፈ ሄሴሜት ታጼኑ
አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች
*እም ተናግሮ ይኄይስ አርምሞ
ከመናገር ዝም ማለት ይሻላል (ዝምታ ወርቅ ነው)
Comments
Post a Comment