⏳ለማን ምን ሰጠህ?
✍️ዶ/ር እዮብ ማሞ
“በምናገኘው ነገር እንኖራለን፣ በምንሰጠው ነገር ደግሞ ሰውን እናኖራለን” - Winston Churchill
💡በአሁን ጊዜ በእጅህ ካለው መልካም ነገር አንዱም እንኳን ከሰዎች መዋጮ ውጪ እጅህ እንዳልገባ እንዳስታውስህ ፍቀድልኝ፡፡ የአንድ ሰው የመወለድ፣ የማደግ፣ የመማርና ሰርቶ የማደር ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር የተሳሰረ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች በሌሎች እርዳታ ኖሩ፣ ተደራጁ፣ ተሻሻሉ፤ ከዚያም በእነሱ እርዳታ ደግሞ ሌላውን አኖሩና አለፉ፡፡ ተተኪዎቹም እንዲሁ ከሌላው የተረከቡትን ይዘው ቀጠሉና ለሌላው አቀበሉ፡፡ ይህ የኑሮ ዑደት ቀጣይና የማያቋርጥ ነው፡፡
⏳እውነታው ሲሰበሰብ፣ ከሌሎች በተቀበልነው ነገር ለመኖር የመቻላችንን ያህል፣ እኛ ደግሞ በምንሰጠው ለሌሎች ሰዎችን እናኖራለን፡፡ ጊዜው መጥቶልን ራሳችንን እስከምንችል ድረስ ለሕልውናችን የተደገፍንበት ሰው እንደነበረ እሙን ነው፡፡ ራሳችንን ቻልን ባልንበት ጊዜ እንኳ አሁም ከሌላው ሰው መዋጮ ውጪ ማድረግ የማንችላቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ አሁን ደግሞ በእኛ ሁኔታ ላይ የሚደገፉ ሰዎች መኖራቸውን ማስታወስ የእኛ ተራ ነው፡፡ በሌላው ሰው ድጋፍ ኖረን በእኛ ድጋፍ ደግሞ ሌላውን የማኖርን ምስጢር እንግፋበት፡፡
💡ትናንት ለማን ምን ሰጠህ? ባለፈው ሳምንት ለማን ምን ሰጠህ? ባለፈው ወር ለማን ምን ሰጠህ! ባለፈው ዓመት ለማን ምን ሰጠህ? ዛሬ ለማን ምን ትሰጣለህ?
⌛️ስጥ! ስትሰጥ ግን ምስጋናን ፈልገን አትስጥ! ስጥ! ስትሰጥ ግን ምላሽን ጠብቀህ አትስጥ! ስጥ! ስትሰጥ ግን ዛሬ መስጠትህ ነገ ትርፍ እንደሚያመጣልህ አስበህ አትስጥ!
❤️
⌛️💡⌛️💡⌛️💡⌛️💡⌛️💡
⏳ What did he give you?
Dr. Eyob Mamo
“We live for what we get, and for what we give we live for.” - Winston Churchill
💡 Let me remind you that none of the good things you have right now are in your hands other than human contributions. A person's birth, upbringing, education and work are closely linked to other people. People lived, organized, and improved with the help of others; Then, with their help, they placed another one and passed by. The successors also took what they had received from the other and handed it over to the other. This cycle of life is continuous.
⏳ When the truth is gathered, as much as we can live by what we have received from others, we give to others as we give. It is true that he was a man who supported us as long as we could. There are still many things we cannot do without the help of others. Now it is our turn to remember that there are people who are dependent on our situation. Let's face it - most people don't know how to say no to money.
What did you give yesterday? What did he give you last week? What did he give you last month? What did you give last year? What are you giving to someone today?
Give it a try! But when you give, do not give thanks! Give! But don't wait for the answer! Give! But when you give, do not think that giving will benefit you tomorrow!
Good Time
❤️
⌛️💡⌛️💡⌛️💡⌛️💡⌛️💡

Comments
Post a Comment