ለውብ ቀን!
💚
በቀደደልህ መስመር አትሂድ የራስ መስመርና የራስ ሀሳብ ይኑርህ
ማሰብ መቻል ታላቅ የፈጣሪ ለሰዉ ልጅ የተሰጠ ስጦታ ነዉ፡፡ይህን ሁሉ ነገር ያስብና
ይተገብር ዘንድ ፣ ባሻዉ መንገድ ይጠቀምበት ዘንድ ፣ መጥፎ ሀሳብና ተግባር እንኳ ቢሆን
የፈለገዉን ያደርግ ዘንድ ፣ ፈጣሪዉ ነጻነትን ሰጥቶታል ብዬ አስባለሁ እኛ ግን በራሳችን
ነፃነታችንን አሳልፈን ለሰዎች ሰጥተናል መልሰው ነፃነታችንንም ሌሎች እንዲሰጡን
እንጠብቃለን ካነበብኳቸው ኤዞፕ ተረቶች ሀሳቤን የሚያጠናክርልኝ አንዱ እንዲህ ይላል።
አንድ የጫማ ዕደሳ ሥራ ላይ የተሠማራ ጫማ ሰፊ ገበያ አልመጣ ብሎት ይቸገራል፡፡
ስለዚህ ጫማ የማደስ ሥራውን ይተውና ..መድኃኒት አዋቂ ነኝ.. ብሎ የህክምና ሥራ ላይ
ይሠማራል፡፡
..ከማናቸውም በመርዝ ከሚመጡ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ መድኃኒቶች በቅናሽ
ዋጋ የሚሰጥ ምርጥ መድኃኒተኛ.. የሚል ፅሁፍ ይለጥፋል፡፡ (በአዲስ መልክ ሥራ ጀምረናል
ከእሱ ይሆን የመጣው?) ሰው እንደ ጉድ ይጎርፍለት ጀመር፡፡ እሱም በየዓይነቱ ቅጠላ
ቅጠል እያመጣ እየቀመመ፤
..አንተ ይሄንን ከኑግ ጋር በማንኪያ ጠዋትና ማታ ውሰድ.. ይላል፡፡ ታማሚው ይከፍላል፡፡
አመስግኖ ይሄዳል፡፡
ሌላዋ:- ትመጣለች
..አንቺ ይሄንን ከሱፍ ጋር አድርገሽ በየሶስት ቀን ውሰጂ.. ይላታል፡፡ አመስግና ከፍላ
ትሄዳለች፡፡
እንዲህ እንዳለ ያ ጫማ ሰፊ ዋና መድኃኒት አዋቂ ተብሎ ዝናው እየገነነ፣ እንደወጥ-ሠሪ
..እጁ አይለወጥም፣ እጁ መድኃኒት ነው፣ እሱ የዳበሰው ሰው ወዲያው ብድግ ነው!..
እየተባለ ጥሩ አድርጎ ራሱን ሸጠ፡፡ አንደበተ-ርቱዕ ስለሆነም አፉ ይጣፍጣል - ሰው ያለውን
ሁሉ ይሰማዋል፡፡ ባንድ ጊዜ ዝና አገኘ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን በጣም ታመመና እቤት አልጋ ላይ ዋለ፡፡ የአገሩ ንጉሥም፤ ባለሟሎቹን
ጠርቶ
..የዚህን መድኃኒተኛ ዕውነተኛ ችሎታ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡ ስለዚህ ሂዱና ያንን እሱ
የመርዝ መከላከያ እያለ የሚሰጠውን መድኃኒት ተቀብላችሁ ከመርዝ ጋር ቀላቅለን
ልናጠጣህ ነው ብላችሁ ንገሩትና ውሃ ብቻ ጨምራችሁ ጠጣ በሉት፡፡ ከዚያ ምን
እንደሚያደርግ መጥታችሁ ንገሩኝ.. አላቸው፡፡
ባለሟሎቹም በንጉሡ በታዘዙት መሠረት ከመድኃኒቱ ጋር መርዝ ሊያጠጡት እንደመጡ
ነገሩት፡፡
መድኃኒተኛው በጣም ደነገጠ፡፡ መርዝ ሊያጠጡት መሆኑን በማሰብም ክፉኛ ተጨነቀ፡፡
ስለዚህ እንዲህ ሲል ዕውነቱን በመናገር ተናዘዘ
..ጌቶቼ፤ እኔ ምንም ዓይነት የመድኃኒተኝነት ችሎታ የለኝም፡፡ የጫማ ዕደሳ ገበያዬ
ሲቀዘቅዝብኝና የኑሮ መላው ሲጠፋብኝ በልቼ የማድርበት አንድ ዘዴ ለመፍጠር ተገደድኩ፡፡
መድኃኒተኛ ሆንኩ፡፡ ህዝቡ ተቀበለኝ፡፡ ቀጠልኩበት.. አለ፡፡
ባለሟሎቹ መድኃኒተኛው ያለውን ወስደው ለንጉሡ ተናገሩ፡፡ ንጉሡ አገሬውን ሰብስቦ፤
..የአገሬው ሰዎች ሆይ! ከእናንተ በላይ ስህተት ላይ የወደቀ ማን አለ? ለዚህ ጫማ ሰፊ
አንዳችሁም ጫማችሁን እንዲያድስ አልሰጣችሁም፡፡ የመርዝ ማርከሻ አድርግልን ብላችሁ
ግን ነብሳችሁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፡፡ ከእንግዲህ ግን ባለሙያ ለዩ፡፡ በስሜት
እየተገፋችሁ በወረት አትነዱ.. ብሎ አጥብቆ አሳሰባቸው፡፡
ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ “ማሰብ የሰውነት መገለጫ ነው”
ሲል ደግሞ አንዱ መስፈሪያ ማሰብ ነው እንጅ ሰው በቀደደልህ መስመር አትሂድ የራስ
መስመርና የራስ ሀሳብ ይኑረን።
ነብስያችሁን አድምጡ!💚 ራሳችሁንም ሁኑ!💚
Beautiful day!
💚
Don't go for less that your full potential
Being able to think is a great gift from the Creator to mankind. He thinks of all this
To act, to use it as it pleases, even if it is a bad idea or action
I think the Creator has given him the freedom to do what he wants, but we ourselves
We give our freedom to people and give it back to others
We look forward to one of the Azop stories I read that reinforces my point.
It is difficult to say whether a shoe repair shop has not come to a large market.
So he quit his shoe repair job and said, "I'm a pharmacist."
It works.
..Deduce special drugs to prevent any toxic diseases
Posts an article titled "The Best Valuable Medicine." (We have started work in a new way
Did it come from him?) The man began to overflow. It is a kind of herb
Bringing and picking leaves;
"Take this with Nug with a spoon morning and night." The patient pays.
Thank you.
The other: She will come
"You do this with wool and take it every three days." Thank you
She is leaving.
That shoe, he said, is becoming more and more popular as a major pharmacist
..The hand does not change, the hand is medicine, the person who touched it immediately jumps! ..
He sold himself well. He is eloquent and his mouth is sweet - what a man has
Everyone feels it. He became famous at the same time.
One day he got very sick and went to bed at home. And the king of the land, The experts
Called
..I want to prove the true potential of this medicine. So go and do that
Take the medicine while it is anti-poisoning and mix it with the poison
Tell him we are going to give you a drink and tell him to drink only water. Then what
Come and tell me what he does.
According to the king's order, the officials came to poison him with the medicine
They told him.
The doctor was shocked. He was very worried that they would poison him.
So he confessed, telling the truth
..My masters: I have no medical skills. My shoe repair market
I had to come up with a way to eat when it got cold and I lost my whole life.
I became a doctor. The people welcomed me. I continued.
The officials took the medicine man and told the king. The king gathered my land,
..O native people! Who has erred more than you? Wide for this shoe
None of you gave me your shoes to renew. Make us poisonous
But you gave up your souls. From now on, identify an expert. Emotionally
He urged them not to drive too fast.
Aristotle, the great Greek philosopher, “reasoned with the body”
And one of the criteria is to think, but do not go in the direction of someone's own
Let's have a line and an idea.
Listen to your soul!
Be yourself! 💚

Comments
Post a Comment