🛑አንድ ሰው ስንት ነው?

(እ.ብ.ይ.)

🔵አንድ ሰው ብዙ ሰው ነው፡፡ ብዙ ሰው ግን አንድ ሰው ሊሆን አይችልም፡፡ የአንድ ሰው ብዙነት ከዕድሜው የሚያገኛቸው ብዝሃ ማንነቱ ነው፡፡ አንድ ሰው በልጅነቱ የልጅነት አስተሳሰብና ማንነት አለው፤ በወጣትነቱም የወጣትነቱን ሰውነትና የትኩስነት ማንነቱን ይይዛል፡፡ ያው አንዱ ሰው ሲጎለምስም የጉልምስና ሰውነትን ያንፀባርቃል፡፡ በአዛውንትነት ዕድሜውም በተረጋጋው ማንነቱ ሰውነቱን ያበጃጃል፡፡ በስተመጨረሻም በዘመነ እርጅናው ትናንቱን እየወቀሰና እያሞገሰ፣ ዛሬ ላይ መካሪና ዘካሪ እየሆነና ወዳለፈው ጊዜ በሃሳብ ፈረስ እየጋለበ፣ ትዝታውንም እያቀነቀነ ወዳማይቀረው ይሄዳል፡፡ እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ማንነቶች በአንድ ግለሰብ ህይወት ላይ ወጥተው የሚገቡ፤ ገብተው የሚወጡ ማንነቶች ናቸው፡፡

🛑አምላክ የሰው ልጅ ተፈጥሮን አንድ ጊዜ ቢሰራውም ሰው ግን ማንነቱን ብዙ ጊዜ ያበጃጃዋል፡፡ እንደእውቀቱ መጠን፤ እንደአስተሳሰቡ ደረጃ፣ እንደሕይወት ገጠመኙ፣ እንደአኗኗር ሁኔታው፣ እንደአስተዳደግ ዘዬው ራሱን ይለዋውጣል፤ አዕምሮውን ያድሳል፤ ሃሳቡን ያገላብጣል፡፡ ከተፈጥሯዊው የእድሜ ጉዞው በተለየም ሰው ዕውቀትን ሲጨምር፣ አስተሳሰቡን ሲያድስ፣ ኑሮውን ሲቀይር አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ሲከተል አዲስ ሰውነትን ይጎናፀፋል፡፡ ያው አንዱ ሰው ብዙ የተለያዩ ማንነቶችን ለራሱ ይጋብዛል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው ስንት ነው? ብዙ ነዋ!

አንድ ጥንታዊ ፈላስፋ ያነሳው ግሩም ጥያቄ ነበር፡፡ ጥያቄውም፡-

🔵‹‹እኔ ራሴ አንድ ሰው ሆኜ አላውቅም፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ እንደህፃን፣ ቀጥሎም እንደወጣት፣ ከዚያም እንደጎልማሳ፣ በመጨረሻም እንደሽማግሌ ኖሬአለሁ፡፡ ከሞት በኋላ ሕይወት ቢኖር እንኳን ዘላለማዊውን ሕይወት እንደማን ሆኜ ነው የምኖረው? የእኔ የሕይወት ተሞክሮ ውጤት ነኝ፡፡ ስለሆነም ሁለትና ሶስት ወይም ከዚያ በላይ የሰው ባሕሪያትን በውስጤ ይዤ በምድር ላይ ከኖርኩ በኋላ ብሞት በምኖረው ሕይወት የመገለጫዬ ባህርይ ማን ሊሆን ነው?›› ሲል ይጠይቃል፡፡

🛑ጥያቄው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ሰው ከሞት በኋላ የማንነት መገለጫው ማን እንደሆነና በየትኛውስ ማንነቱ ሊፈረጅ እንደሚገባ ማወቅ አጓጊ ነው፡፡ እንደእኔ ግን ሰው ከሞት በፊት በመጨረሻ ሕይወቱ የያዘው ማንነቱ በዕድሜው ሙሉ ያያቸውና የተለዋወጠባቸው ማንነቶች ድምር ውጤት በመሆኑ የሚፈረጀውም፣ የሚከሰሰውም፣ የሚደነቀውም ሆነ የሚከበረው በኋለኛው የህይወት ማንነቱ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨረሻው ሕይወቱ የዕድሜው ሁሉ መጠቅለያ ማንነት ነው፡፡ ሰው በዕድሜው ካያቸው የራሱ የተለያዩ ማንነቶች የሚወሰደውን ወስዶ፣ የሚጣለውን ጥሎ መልካሙን ማንነት መያዝ የእሱ ድርሻ ነውና፡፡ ከራስ መማርን የመሰለ ምን ወሳኝ ትምህርት አለ?! ምንም!

🔵እድሜ ካልተማርንበት ቁጥር ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ቁጥር ብቻ ደግሞ ዋጋ የለውም፡፡ ዋጋ ያለው ሕይወት እውን የሚሆነው የሰው ልጅ ዕድሜ በበጎ ስራ ሲቆጠርና ሲተመን ብቻ ነው፡፡ በዚች አስገራሚ ዓለም ሽማግሌ ሆነው እንደ ልጅ የሚኖሩ፤ ልጅ ሆነው እንደአዋቂ የሆኑ መኖራቸው ሃቅ ነውና፡፡

🔴ከሞት መለስ በሕይወት እያለ የሰው ልጅ መጠየቅም፣ መኮነንም፣ መደነቅም ሆነ መከበር ካለበት በአሁናዊው ማንነቱ ነው፡፡ ዛሬ ማንነቱን በበጎ አስተሳሰብ የዋጀ ሰው ትናንት ባጠፋው መወቀስ የለበትም፡፡ የትናንቱ ጥፋት በትናንት ማንነቱ ነው ሊፈረጅ የሚገባው፡፡ ዛሬ አዲስ ሰው ነውና!

🔵የአመክንዮ ሕግም በትናንት ማንነቱ የዛሬውን አዲስ ማንነቱን የሚደመድሙ ሰዎች ልክ እንዳልሆኑ ይናገራል፡፡ ይሄንንም Miss-representation Fallacy ሲል ይገልፀዋል፡፡ ዛሬ አዲስ ሰው ነውና የትናንቱን ሽሯል፡፡ የትናንት አሮጌ አስተሳሰቡን በአዲስ አስተሳሰብ አድሷል፡፡ የትናንት አላዋቂነቱን በዛሬ ዕውቀቱ ቀይሯል፡፡ ትናንት ያልገባው ዛሬ ገብቶታልና፡፡

ታላቁ የነፃነት ታጋይ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ይሉናል፡-

🔷‹‹በስኬቴ አትዳኙኝ፡፡ ይልቁንስ ምን ያህል ጊዜ ወድቄ ምን ያህል ጊዜ መልሼ እንደተነሳሁ አይታቹህ ፍረዱኝ (Do not judge me by my success, judge me by how many times I fell down and got back up again)››  ይላሉ፡፡

♦️አዎ! የአወዳደቅህ ሳይሆን የአነሳስህ ሁኔታ ያንተን ማንነት አጥርቶ ያሳያል፡፡ የወደቁ ሳይሆን ከውድቀታቸው የተነሱ አዕምሯቸው ሰፊ ስለመሆኑ ክርክር አያሻውም፡፡ በጠባቡ አስተሳሰባቸው ወድቀው በሰፊ አስተሳሰባቸው ሕይወታቸውን ያሰፉና ከውድቀታቸው የተነሱ ትንሳኤ ብሩሃን የሆኑ ሊደነቁ ይገባል፡፡ ምክንያቱም በመውደቅ መነሳታቸው መካከል ያገኙት ትምህርት እንዴት ከውድቀት መነሳት እንደሚቻል አዲስ ዕውቀት አስጨብጧቸዋል፡፡ ተስፋ ቆርጠው ወድቀው አለመቅረታቸው የሚያሳየው የአስተሳሰባቸው ጮራ ምን ያህል የበራ እንደነበረ የሚያሳይ ነውና፡፡

🔷አዎ! ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን በተለያዩ ውድቀቶችና አወዳደቆች ተፍገምግመናል፡፡ የሚያሳፍረውና የሚያስፈራው ነገር ከውድቀታችን ለመነሳት ፍላጎቱም ሆነ ቁርጠኝነቱ የሌለን መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዶች በዘረኝነት ወድቀዋል፣ ጥቂቶች በትእቢት በአፍጢማቸው ተተክለዋል፡፡ ቀላል ቁጥር የሌላቸው አወቅን ብለው ደንቁረዋል፤ ሰፋን ብለው ጠብበዋል፡፡ ሰለጠንን ያሉት እቡያን ሰይጥነዋል፡፡ ከዕድሜአቸው ያልተማሩ፤ ከብዝሃ ማንነታቸው ቀለም ያልቆጠሩ፣ መልካሙን ያልኮረጁ ቆመ-ቀሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ከብዝሃ ማንነታቸው ያልተማሩ በአንዱ ማንነታቸው የሙጥኝ ያሉ አዲስ ሃሳብ ያስደነግጣቸዋል፤ ለውጥ ይቀፋቸዋል፤ አዲስ ማንነት ያስፈራቸዋል፡፡

♦️አዎ! አንድ ሰው ብዙ ነው፡፡ ብዙነቱን ግን እውን የሚያደርገው በሰፊው አስተሳሰቡ ሲሰፋ ነው፡፡ ከተፈራረቁበት ማንነቶቹ ጠቃሚውን ማንነት ፈልቅቆ የሚያወጣ ብልህ ሰው ከብዙነቱ እልፍ ትምህርት ቀስሟል፡፡ ቅስሙን የሚሰብር ሳይሆን ቅስሙን በአዲስ አስተሳሰብ የሚጠግን ጀግና ካለፈው ሕይወቱ ብዙ የተማረ ነው፡፡ ከውድቀቱ የሚማር መላልሶ መነሳት አይቸግረውምና፡፡

🔷ወዳጄ ሆይ… አንተ አንድ ሰው አይደለህምና እንደብዙ ሰው አስብ የዕለቱ መልዕክት ነው! መውደቅን አትፍራ! ነገር ግን እንዴት ከወደቅበት ቦታ መነሳት እንደምትችል አዕምሮህን አሰራ፡፡ መውደቅ በማንም ላይ የሚደርስ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ ወድቆ መቅረት ነው አሳፋሪው ነገር፡፡

      ቸር መነሳት!

✍️እሸቱ ብሩ ይትባረክ
🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑

How much is a person?


🔵 One person is many people. But many people cannot be one person. A person's diversity depends on his or her age. One has a childhood mindset and identity; As a young man, he possessed a youthful body and a warm personality. The same can be said of adulthood. In his old age, he adapted his body to a stable body. Eventually, in his old age, he goes to great lengths to denounce and glorify the past, to become a mentor and mentor today, and to ride on the horse of the past, reminiscing about his memories. All these different identities come into one's life; They are identities that come in and out.

🛑 God created human nature once, but man often changes his identity. According to his knowledge: It changes according to the level of thought, the experience of life, the way of life, the way of upbringing; It refreshes the mind, He inverts the idea. Unlike natural life, a person acquires a new body when he or she acquires knowledge, renews his or her mind, and changes his or her life. The same person invites many different identities. How much is a person? Lots of it!

An ancient philosopher asked a wonderful question. The question is:

🔵 “I have never been a person myself. Because I lived first as a child, then as a teenager, then as an adult, and finally as an adult. Even if there is life after death, who am I to live forever? I am the product of my life experience. So, if I have two or three or more human qualities in me and I live on earth, who will be my character in my life? ”

🛑The question is an important question. It is interesting to know who a person's identity is after death and what his or her identity should be. But for me, the last thing a person has before his death is the sum of the identities he has seen and changed throughout his life, and he will be judged, accused, admired and respected in his later life. Because his last life was the culmination of his life. It is his responsibility to take what is different from what he sees in his own age, to discard what is thrown away, and to retain what is good. What is an important lesson like self-learning ?! nothing else!

🔵 It only happens when we are uneducated. Only numbers are worthless. Valuable life is possible only when human life is counted and valued. Living as old men in this wonderful world, It is a fact that they are children and adults.
After death back, if human beings are to be questioned, judged, admired or respected, it is in their current state. A person who redeems his identity today should not be blamed for what he did yesterday. Yesterday's crime should be classified as yesterday's. He is a new man today!

ሕThe law of logic says that those who conclude his new identity yesterday are wrong. He describes this as Miss-representation Fallacy. He is a new person today and canceled yesterday. He revived yesterday's old thinking with a new mindset. He changed yesterday's ignorance with today's knowledge. What he did not understand yesterday is understood today.

The great freedom fighter Nelson Mandela tells us:

🔷 “Don't judge me by my success. Instead, judge me by my success, judge me by how many times I fell down and got back up again.

♦ ️ Yes! Your motivation, not your failure, is a clear indication of who you are. There is no need to argue that their minds are wide open, not those who have fallen. The resurrection of those who fell short of their narrow-mindedness, expanded their lives, and rose from their fall should be admired. Because the lessons they learned in the middle of the fall gave them new knowledge of how to rise from the fall. The fact that they did not give up shows how bright their minds were.

🔷Yes! Many of us today have been through a series of setbacks. What is embarrassing and frightening is that we do not have the desire or commitment to rise from our fall. Some have fallen into racism, some have been planted with pride. Countless people are ignorant. They are narrow and narrow. The trained ones are satanic. Uneducated; Consider homeless people who are not colorful, who do not imitate good manners. Those who are not educated in their diversity are shocked by new ideas that cling to one another; They hate change; They are afraid of a new identity.

♦ ️ Yes! One person is many. But the multiplicity is realized by the expansion of his broad thinking. The wise man who learned the ins and outs of his identity learned many lessons. A hero who does not break his heart but corrects his mind with a new mindset has learned a lot from his past life. He who learns from the fall will not have a hard time getting up.

🔷 My friend… You are not one person Think like most people is the message of the day! Do not be afraid to fall! But think about how you can get up from where you fell. Falling happens to anyone. Instead, it's a shame to fall.


🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑🔵🛑


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው