ሕይወት በብዙ አጋጣሚዎች የተሞላች ናት። 

አንዳንድ ጊዜ የምንወደውን ነገር እጃችን ገባ ስንል በምን ፍጥነት እንኳን እንደሆነ ሳናውቀው ከእጃችን ሲሾልክ እናየዋለን። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እጅግ ያልጠበቅንው ነገር እጃችን ሲገባ እናየዋለን። እንግዲህ ሕይወት በብዙ ተቃራኒ ነገሮች የተሞላች ናት። ማግኘትና ማጣት፣ መሄድና መምጣት፣ መውጣትና መግባት፣ መኖርና መሞት፣ መሙላትና መጉደል፣ መፈለግና መገፋት የነበሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ናቸው።

ሕይወት በአንድ ነገር ስታስለቅሰን በሌላው ደግሞ ትክሰናለች። በአንዱ ስታሳዝነን በሌላው ደስታን ታጎናጽፈናለች። ሕይወት ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ መንገድ አላት። ከእኛ የሚጠበቀው ተስፋ ማድረግና ማመን የሚሆነውን በትዕግስት መጠበቅ ሲሆን በሚከሰቱብን ነገሮች ሁሉ ከማማረር ይልቅ አመስጋኝ መሆንና ለበጎ ነው ማለትን መልመድ ይኖርብናል።
..............


 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው