የአንቺ ነው እናቴ
አንቺ እየከሳሽ እኔ መፋፋቴ
አንቺ አጎንብሰሽ እኔ መቃናቴ
ተርቦ አንጀትሽ ጠግቤ መብላቴ
ባዶ እግርሽን ሆነሽ እኔ መጫማቴ
አንቺ አፍሽ ደርቆ እኔ መጠጣቴ
አንቺ ሳትማሪ ተምሬ ማወቄ
ልፋትሽ ተረስቶ እኔ መደነቄ
እውቀትና ክብሬ ስጦታ ውበቴ
ሽልማት ማዕረጌ መልኬ ደምግባቴ
የእኔ እኮ አይደለም የአንቺ ነው እናቴ።
አንቺ አጎንብሰሽ እኔ መቃናቴ
ተርቦ አንጀትሽ ጠግቤ መብላቴ
ባዶ እግርሽን ሆነሽ እኔ መጫማቴ
አንቺ አፍሽ ደርቆ እኔ መጠጣቴ
አንቺ ሳትማሪ ተምሬ ማወቄ
ልፋትሽ ተረስቶ እኔ መደነቄ
እውቀትና ክብሬ ስጦታ ውበቴ
ሽልማት ማዕረጌ መልኬ ደምግባቴ
የእኔ እኮ አይደለም የአንቺ ነው እናቴ።

Comments
Post a Comment