#የተጎዳ_ልብ ክፍል_8_እና_መጨረሻው


#የተጎዳ_ልብ
#ክፍል_8_እና_መጨረሻው
#እውነተኛና_አስተማሪ
የሰላም ማርገዝና የፍፁም መጥፋት ያሳሰባቸው እናትና ልጅ ተቃቅፈው ከተላቀሱ በኋላ እማማ የሺ ግን እንዴት ከፍፁም ጋር ይህ ሊፈጠር ቻለ ስትል ጠየቀች ሰላምም እራሷን ለማረጋጋት እንባዋን እየጠረገች በረጅሙ ከተነፈሰች ቡሃላ እማዬ እኔ ፍፁምን አፈቅረዋለሁ አለች እማማም ድንግጥ እንደማለት ብለው ልጄ እሱኮ በሴት ልጅ ስለተጎዳ... ብለው ንግግራቸውን ሳይቋጩ አውቃለው እማዬ ግን ፍፁሜ ሁሉን እረስቶ ከልቡ አፍቅሮኝ ነበር ግን እኔም እንደዛች ሴት ሌላ አግብቼ ዳግም ልቡን ሰበርኩት አለች ይሄኔ እማማ የሺ ከልብ ተፀፅተው እያለቀሱ አይ እድል የኔ ያሮጊቷ እድል ልጆቼን አሳጣኝ ይሄ የኔ ጥፋት ነው ብለው እድላቸውን ማማረር ጀመሩ.... ከዛም ስለመሸ ሰላም ተነስታ ወደ ባልዋ ሄደች ...
ፍፁም ኑሮውን ከአዲስ አበባ ውጪ ካረገ ሰንበትበት ብሏል ግን እዛም ሆኖ ሰላምን መርሳት አልቻለም እማማንም ጥሎ መሄዱ እረፍት ነሳው እናቱን ጥሏት ሲሄድ እንደሞተችበት ሁሉ አሁን አሉኝ የሚላቸው ሰላምና እማማ የሺ የሚሞቱበት መሰለው ይሄኔ ለመጨረሻ ግዜ አይናቸውን አይቶ እራሱን ለማጥፋት ወሰነ ይህን የወሰነው ደግሞ ከንግዲህ ማንንም ማጣት ስለማይፈልግ ነው...
ይህን በወሰነ 3ኛው ቀን ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ እማማ የሺ ጋር ሄደ እማማ የሺም ልክ ሲያዩት አይናቸውን ማመን አቃታቸው እንደህፃን ዘለው ተጠመጠሙበት ... ትንሽ ከቆዩም ቡሃላ እማማ የሺ የሰላምን ማርገዝ ነገሩት ይሄኔ ከሰውየው መስሎት ፊቱ ላይ የሀዘን ጥላ ሲያጠላ ታያቸው እሳቸውም መለስ አርገው ልጄ ካንተኮ ነው አሉት ይሄኔ ምን እንዳስደነገጠው ባያውቅም በድንጋጤ ብድግ አለ ... ከብዙ ሰአት ቡሃላ ተረጋግተው ማሰብ ጀመሩ...
ፍፁም የሰላምን ሰላም ማጣትና ከማትፈልገው ሰው ጋር እንድትኖር መፍቀድ ሲያቅተው የተወለደበት ሰፈር የእናቱን ምትክ እማማን ወስዶ ተከራይቶ አስቀመጣቸው ከዛም ሰላምን የመጣው ይምጣ ብሎ ይዟት ጠፋ... ለተወሰነ ግዜ አራጣ አበዳሪው ሰውዬ ቢያስፈራሯቸውም ልጁ ተወልዶ DNA ምርመራ የፍፁም መሆኑን ሲያውቁ ተስፋ ቆርጠው የማማ የሺን ደሳሳ ጎጆ አፍርሰውባቸው ተዋቸው።
ባሁን ሰአት ሰላም ወልዳ ፍፁምን ደስተኛ አድርጋዋለች እማማ የሺም ከልጅም አልፎ የልጅ ልጅ በማየታቸው ከልክ በላይ ደስተኛ ሆነዋል...
።።።።።።።።። #አበቃሁ።።።።።።።።።።

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች