#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_2


#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_2
 #እውትተኛና_አስተማሪ !!!!
ፍፁም አፍቅሮ ባመናት ሴት መከዳቱ ብቻ ሳይሆን ከእናቱ የፍቅረኛው ደስታ በልጦበት እናቱ በደካማ ጉልበቷ ለፍታ ለከፉ ቀን ብላ ያስቀመጠችውን ገንዘብ መንካቱ ህሊናውን እረበሸው የእናቱንም አይን ማየት አሳፈረው ይኔና ወደቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ጓደኞቹ መሄድን መረጠ በርግጥ ፍፁም ጓደኞቹ በሙሉ ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸውና አልፎም ቤት የሌላቸው ነበሩ ፍፁምም ስለ ልጅቷ እያሰበ እየተበሳጨ ስለነበር በረንዳ የሚያድሩት ጓደኞቹ ለብርድ ብለው የገዙትን አረቄ ጠጣው ይሄኔ ያለመደ ጨጓራው አሲድ እንደነካው ገላ ተንገበገበ...
እንደዛ ተሰቃይታ እያሳደገች ነገ ልጄ ትምርቱን ጨርሶ ያሳልፍልኛል ብላ የምታስብ እናት በልጇ በድንገት መጥፋት በድንጋጤ ታመመች ሀኪም ቤት እንዳትሄድ ልጇ ለክፉ ቀን ያኖረቻትን ገንዘብ ወስዶባታል ጉዳይ የማይሰጠው አባት አረቄውን ልፎ ለጠገበ ጎረምሳ አልጨነቅም ሲል ነገር አለሙን ትቶታል... ቀናቶች እየሄዱ ሳምንት ላይ ደረሱ እናትም አቅሟ ስለደከመ ከዚ በላይ መቆየት አልቻለችም የልጄን አይን ልይ እንዳለች አረፈች...
ፍፁም ከምንም በላይ የምትበልጥበትን እናቱን ባለማስተዋል አጣት ለፍቅር ብሎ ያጠፋው ጥፋት እናቱን ነጠቀው ፍፁም የእናቱን መሞት በሰማ ግዜ ክፉኛ ነበር ያዘነው ከዛ ግዜ ቡሃላ በሴቶች ላይ ቂም ያዘ የመጀመርያ እርምጃው ስራ መስራት መጀመር ነበር ወላጅሽአባቱ በህይወት መኖሩን በራሱ ከምንም አይቆጥረውም ... ከጨርቆስ በሀዘን የተጎዳ ልቡን ብቻ ይዞ ወደ ፒያሳ ሰፈር ቀየረ ከዛም ጋራጅ ገብቶ በረዳት መካኒክነት ስራ ጀመረ ...
ፍፁምን ላየው በጭራሽ የተጎሳቆለ አይመስልም ቆንጆ ነው በዛ ላይ በየለቱ በስፖርት የዳበረው የሰውነት ቅርፁ ወንዳወንድነትን አላብሶታል... ለዛም ማንኛዋንም ሴት ማማለል ይችላል በረፍት ቀኑ ሲኒማ ይገባል ማታ ከስራ ቡሃላ ጥሩ አለባበስ ለብሶ ወክ ያደርጋል ይሄኔ ሴቶች አይናቸውን ይጥሉበታል ፍፁምም የሚፈልገው ይሄን ነበር...ለበቀል
አንድ ቀን አንዲት 20 አመት እንኳ በቅጡ ያልሞላት ቆንጆ መኪና ተበላሽቶባት መጣች ይሄኔ ፍፁም ገና የስራ ልብሱን ለመቀየር እየተዘጋጀ ነበር ገና ስታየው ልቧ ደነገጠ ወደደችው እሱም ኩራቱን ጀመረ ብዙ ደጅ ከጠናች ቡሃላ እሺ ብሏት ፍቅር ጀመሩ ፍፁም እሷን የቀረባት አፍቅሯት ስላልነበር ከልብ እንድታፈቅረው ማድረጉን ቀጠለ ... በፍቅር ለወራት ከቆዩ ቡሃላ አረገዘች... ይሄኔ ፍፁም የሚፈልገው ተሳልካለት አረገዝኩ ስትለው አላቅልሽም አላት በመጀመርያ እየቀለደ መስሏት ነበር ነገር ግን ፍፁም ስልኳን ባለማንሳትና ከሷ በመሸሽ ተስፋ አስቆረጣት...
#ይቀጥላል...

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው