#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_1


#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_1
 #እውትተኛና_አስተማሪ
ፍፁም ይባላል 12 ክፍል ተማሪ ነው ፍፁም ወዶ ሳይሆን ተገዶ ሲሆን የሚማረው በህይወቱ እንደትምህርትና እንደ ወላጅ አባቱ የሚጠላው ነገር የለም ፍፁም ለወላጅ እናቱ ሲል ነው የሚማረው እናቱ በጣም ምስኪንና ድሃ ነች ባሏ ማለትም የፍፁም አባት ጥበቃ ሲሆን የሚሰራትን ከመጠጥ የተረፈች ከቤት ክራይ የማታልፍ ገንዘብ ለቀለብና ለተለያዩ ወጪዎች ስለምታንሳት ጉሊት በመቸርቸር ልጇን ታስተምራለች ፍፁም ይሄ ያስፈልገኛል ካለ ከየትም ብለው ተበድረውም ይሁን ተርበው ያደርጉለታል ታድያ ሁሌም የፍፁም እናት ልጃቸው ተምሮ ትልቅ ደረጃ እንዲያደርሳቸው ታስጠነቅቀዋለች ለዚም ነው በግድ ትምህርት ቤት ደርሶ የሚመለሰው...
ፍፁም ተወልዶ ያደገው ጨርቆስ አካባቢ ሲሆን ለናትና አባቱ 1 ነው በርግጥ ታናሽ ተወልዶለት ነበር ነገር ግን ብዙም ሳትቆይ ነበር ወደ ፈጣሪዋ የተመለሰችው ብዙ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የፍፁም አባት መጠጥ ጠጥተው እየገቡ መረበሽ የጀመሩት ከዛ ቡሃላ ነበር ግን ፍፁም አባቱ ሲሰክር እናቱን ስለሚረብሻት ፍፁም አባቱን በጣም ይጠላዋል ፍፁም እንደማንኛውም ልጅ አይደለም ጠዋት ተነስቶ ለእናቱ ጉሊት የምትሸጣቸውን እቃዎች ያደርስላታል ከዛም የቤቱን ስራ ባግባቡ ሰርቶ ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳል... ይህ ሁሉ ሲሆን ፍፁም እንደ እኩዮቹ መጥፎ መንገድን አልሄደም ነበር ከወንድ ጓደኛ ውጪ ስለሴት ማሰብም አይፈልግም ... ግን 12 ክፍል አጋማሽ ቡሃላ ለፍፁም እንግዳ ነገር ገጠመው...
አንድ ቀን በጥዋት ተነስቶ ለእናቱ እንደተለመደው እቃዎቹን ሊያደርስላት ሲሄድ በትከሻው ከያዘው ተጨማሪ በእጁ ፊስታል አንጠልጥሎ ይዟል ይሄኔ አንዲት ነጠላ የለበሰች እድሜዋ ከሱ ብዙም የማይርቅ ሴት ላግዝህ ስትል በእጁ ያንጠለጠለውን ፌስታል ተቀበለችው እሱም ስለከበደው በሰአቱ አልተግደረደረም ነበር በሁለቱ መሃል ማንም ምንም ሳይተነፍስ ዝምታ እንደሰፈነ የእናቱ ቦታጋ ደረሱ...ሊያመሰግናት ቃል አጠረው ሳያስበው እቅፍ አርጎ አስቸገርኩሽ አይደል አላት እሷም ሁኔታው እንደመደንገጥ እያረጋት አይ ችግር የለውም አለች ድምጿ ከንግግሯ ለዛ ጋር ተደምሮ ደጋግማ ብታወራ ያስብላል አይቷት መልሶ አቀረቀረ ሄዋን እባላለው አለችው ፍፁም አላት ስሙ የጠፋበት ይመስል ብዙ አስቦ በጣም ታምራለች ሴት ልጅ የቱንም ያህል ብታሸበርቅ ግድ የማይሰጠው ፍፁም ዛሬ ተረታ ... ከልጅቷ ጋርም በዚች ገጠመኝ የተጀመረው ፍቅር ይበልጥ እያማረበት ሄደ...
ይሄኔ እናቱን ማገዝ ላይ ቀዘቀዘ ብዙ ግዜውን ለፍቅረኛው ሄዋን ይሰጥ ጀመር ሄዋን ባንፃሩ ሀብታም ቤተሰብ አላት የኮሌጅ ተማሪ ናት ... ይህ በንዲህ እንዳለ ታድያ የሄዋን ልደት ይደርሳል ... ፍፁምም ምንም ገንዘብ ስለሌለው በምን ሰርፕራይዝ ላርጋት ብሎ ይጨነቃል ጓደኞቹን ሲያማክርም ሀሀሀ የህንድ ፊልም እያየህ ተበላሸህ አይደል እያሉ ይስቁበታል እሱም በነሱ ንዴት እናቱ ለክፉ ቀን ከምታስቀምጥበት ፍራሽ ስር በርብሮ ያገኛትን ይዞ በመውጣት ለፍቅረኛው ትወደዋለች ያለውን የብር ሀብል በመግዛት ይምትማርበት ኮሌጅ ድረስ ያመራል በሩ ላይ ሲደርስም ከሰው ጋር ቆማ ስላያት በስልኳ ደወለ አንስታ ሄሎ ይቅርታ እቤት ነኝ አባቢ ስላለ ቡሃላ እደውላለው ብላ ጆሮው ላይ ዘጋችበት ፍፁም የማያውቃት ሴት መሰለችው በአይኑ እያያት ዋሸችው ቆሞ መጨረሻዋን ያይ ጀመር ...
ከደቂቃዎች ቡሃላ ሴቶቹን ተሰናብታ ከአንድ ወንድ ጋር መኪና ውስጥ ገብተው ሄዱ ፍፁምም የሚያየውን መገመት አልፈለገም እሩጦ ሴቶቹጋር ሄደና ሄዋን አብሯት ያለው ማነው አለ እነሱም ከት ብለው ስቀው ልትደረብ አማረህ ባሏ ነዋ አሉት ለዛ ቢስ በሆነ ንግግር የሚያረገው ጠፋው በንዴት የገዛላትን ሀብል በጣጠሰው....
#ይቀጥላል...

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው