ምክር ለወዳጄ !
(Sewagegn At.)

በምድር ላይ የማይታለፍ ፈተና የማይወገድ ችግር አለ ብለህ አትመን፡፡ አሁን ከሚያስጨንቅህ ችግር ይልቅ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ መፍትሔ ከውስጥህ አለ፡፡ እመን! አሁን ከከበደህ ፈተና በላይ በብዙ እጥፍ የሚልቅ መፍትሔ አለህ፡፡ ፈተና ችግር የሚሆነው ተጋፍጠው ማለፍ ለማይችሉት መፍትሔ የለሾች ብቻ ነው፡፡ ከፈተናና ከችግር መማር እንጅ መማረር አይጠቅምም፡፡

 በትናንት ፈተና በዛሬም ችግር መጸጸት ትርፉ ነገን ማበላሸት ነው፡፡ ለሚያስተውል እንደፈተና ያለ ድንቅ መምህር የለም፡፡ እንደችግርም መካሪ አይገኝም፡፡ ለየትኛውም ችግር መፍትሄን ከሌላው ብቻ አትጠብቅ። መፍትሄው እኔ ብቻ ነኝ ብለህም አትታበይ። ያንተን ድርሻ ካልተወጣህ መፍትሄው ምሉዕ አይሆንምና ድርሻህን ለመወጣት ድከም። ስንፍናን አርቅ። ችግር ሳይሆን መፍትሄን ለመጨመር በርታ !

የታናሽህን ምክር አትናቅ!

ሰላምና ጤና ይብዛልህ !

 

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው