ነገረ "ርቀት"
...
.
በሽታ በመዳፍ፣
በሚዘገንበት፣ በዚህ ክፉ ዘመን፤
ሁሉንም አትጨብጥ፣
ደጋግመህ ታጠበው፣ እጅህን አትመን።
...
የምትስበው አየር፣
እንዲሁም ወደውጭ፣ የምትተነፍሰው፤
ተውሳክ ቢኖረውስ?
አፍ አፍንጫን ጠብቅ፣ ሸፍነው አንተ ሰው፤
ሀገር አማን መስሎህ፣
በሽታን እንዳትምግ፣
ለደግ ወገንህም፣ ሞት እንዳታወርሰው።
...
ተቃቅፎ መሳሳም፣
ተጠጋግቶ መቆም፣
የቆዬ ልማድህ፣ ቢሆንም ባይሆንም፤
አሁን ላይ አይሆንም፣
እንዲህ ያለው ፍቅር፣ ከሞት አያድንም፤
ግድ የለም ራቀው፣
ለጊዜው ይቅርብህ፣ አስብ ለወዳጅህ፤
ምን ብትነፋፈቅ፣
በፍቅር የቀና፣ ሞት ቆሟል ከደጅህ።
.
ምን ታደርገዋለህ፣
አምኖ ማቀፍ ቀረ፣ ያንንም ይህንም፤
አየህ ቀን ሲከፋ፣
እንኳን ጥል ጥላቻ፣ ፍቅር አይታመንም።
.
.
እንዲያው ለነገሩስ፣
እንኳን ለኮሮና፣ ሆኖ መድኃኒቱ፤
በክፉዎች ዘመን፣
ከሰው ራቅ ማለት፣
አ ያ ጠ ራ ጥ ር ም ፣ ሰላም ጤንነቱ።
.
.
ሰው መራቅ ከበደህ?
ዘመን አይክፋ እንጅ፣
የማይቻል የለም፣ ልመደው ዘመዴ፤
ሞት ያዘለ ነገር...
አንተ ባትሸሸው፣
እስከመጨረሻው፣ ያ ር ቅ ህ የለ እንዴ !?!

Comments
Post a Comment