←↑↓→
በዚህ ሁሉ መሐል...
አሁንም ሰው አለ፤
አሁንም ሕዝብ አለ - በጽናት የቆመ፤
ሀገር እንዳትወድቅ - እንደተሸከመ፤
(ያውም ክንዱ እስኪዝል፣ ብዙ እየታመመ።)
↑↓↑
ምን የችግር ብዛት፣ ቢወርድ እንደ ናዳ፤
ንፁሃን ቢሰውም፣ ለትውልዱ ዕዳ፤
ጥቂት ብርቱ ካለ፣ በጽናት የሚቆም፤
መቃናቷ አይቀርም፣ ሀገር ምን ብታዘም።
=→
ፈታኝ ወቅትን ማለፍ፣ ቢከብድም ባይከብድም፤
የመስዋዕት ምድር፣ ከከፍታ አትወርድም።
→←

Sewagegn At.

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው