"ሰውነት" !
...
"ሕዝበ አዳሜ ሁሉ፣ ሰው እየመሰለ፤
በሰዎች ወንበር ላይ፣ ተቀምጦ የዋለ፤
በሰውነት መስፈርት፣ አሁን ሰው የት አለ?"
ብዬ ለመናገር፣ ምላሴን ሳስዬ፤
ለማውጣት ስጀምር፣ ድምፅ ከጉሮሮዬ፤
"ቆይ ግን አንተስ ሰው ነህ?" አለኝ ሕሊናዬ።
---
ሰውነት ሲከዳ...
ከሰብዓዊ ዓለም፣ ሰይጣን ይወለዳል፤
በመሰይጠን ዘመን፣
ከምንም ከምንም፣ ሰው መሆን ይከብዳል።
-----//-----)
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች
የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች.....#share *ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ ነቢይ በሀገሩ አይከበርም። *መዐር አይጥዕሞ ለአድግ ለአህያ ማር አይጥማትም *አድኅን ርእስከ ራስህን አድን *አፍ ይጼውአ ለሞት አፍ ሞትን ይጠራል *ለሰሚዕ እጽብ ለሰሚው አስደናቂ *ብላዕ በሐፈ ገጽከ ጥረህ ግረህ ብላ *አክብር አባከ ወእመከ አባትና እናትህን አክብር *ተፋቀሩ በበይናቲከሙ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ *ኀላፊ ንብረት፣ክመ ጽላሎት ሀብት እንደ ጥላ አላፊ ነው *እምነ ረሃብ የኄይስ ኩይናት ከረሀብ ጦርነት ይሻላል። *ለዘየአምን ኩሉ ይትከሃል ለሚያምን ሁሉ ይቻላል *ሕማማ ለዐይን ርዕየተ ጸላኢ ያይን በሽታዋ ጠላትን ማየቷ *እለ ከርሦሙ አምላኮሙ ሆድ አምላኪዎች *ሀብ ለኩሉ ለዘሰአለከ ለለመነህ ሁሉ ስጥ *በቁስለ ዚአሁ ሀዮነ ቁስለነ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን *አኮ ለዘሮጸ ባህቱ ለዘበደረ ለሮጠ አይደለም ለቀደመ እንጅ *አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ *እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንእት ፍቅር እንደሞት ጽኑ ናት። *ሕይወት ወሞት ውስተ እደ ልሳን ህይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ *መኑ ከመ አምላከነ? እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን አለ? *አኮ በሲበት አላ በአእምሮ በሽበት አይደለም፤በማስተዋል እንጅ *ህብ ፍኖተከ ለእግዚአብሔር መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ *ሀቡ ዘነጋሢ ለነጋሢ፤ወዘተረፈእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የቄሳርን ለቄሳር፤የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ። ...
Comments
Post a Comment