ከሰሞኑ በሰደድ እሳት እየነደደ ስለሚገኘው የአማዞን ደን
“ከ340 ነባር ጎሳዎች መካከል 100 ጎሳዎች ተገናኝተው አያውቁም፡፡”
“80 በመቶ የሚሆነው የአለማችን ምግብ በአማዞን የበቀለ ነው፡፡”
አዲስ ሚድያ ኔትወርክ(ኤ ኤም ኤን ) ነሃሴ 21፤2011
ከሰሞኑ በሰደድ እሳት እየነደደ ስለሚገኘው የአማዞን ደን አንዳንድ መረጃዎች፡
ከሰሞኑ በሰደድ እሳት እየነደደ ስለሚገኘው የአማዞን ደን አንዳንድ መረጃዎች፡
• አማዞን የአለማችን ትልቁ ደን ሲሆን 40 በመቶ በሚሆኑት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ላይ አርፏል፡፡
•ጥቅጥቅ ደኑ 9 ሃገራት ላይ የሚያርፍ ሲሆን 2/3ተኛው ወይም 60 በመቶው የአማዞን ክፍል የሚገኘው ብራዚል ነው፡፡
•ስፋቱ የህንድን ሁለት እጥፍ ያክላል፡፡
•አማዞን ሃገር ቢሆን ኖሮ የአለማችን 9ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር፡፡
•በደኑ ውስጥ ከ30ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይኖራሉ ከነዚህ ውስጥ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ እና 2ሺህ አባላት ያላቸው 350 ነባር ጎሳዎች ይገኙበታል፡፡
•ከ350 ነባር ጎሳዎች መካከል 100 ጎሳዎች እርስ በእርስ ተገናኝተው አያውቁም፡፡
•አማዞን በአለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥቢ አንስሳት፤አዕዋፋት እና በደረት የሚሳቡ ፍጡራን የሚገኙበት ደን ነው፡፡
•በየሁለት ቀናት ልዩነት አዳዲስ የእጽዋት ወይም የእንስሳት ዝርያዎች በአማዞን ይፈጠራሉ፡፡
•40 ሺህ የእጽዋት እና 1300 የአዕዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡
•በጥቅጥቅ ደኑ 400 ቢሊዮን ዛፎች ይገኛሉ፡፡
•የአለማችን 20 በመቶ ኦክስጅን የሚመረተው በአማዞን ደን በመሆኑ “የፕላኔታችን ሳንባ ” በመባልም ይታወቃል፡፡
•አማዞን ከ90 እስከ 140 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን በውስጡ በመያዝ የካርቦን ልቀቱን ይቆጣጠራል፡፡
•80 በመቶ የአላማችን ምግብ በአማዞን የበቀለ ነው፡፡
•120 የሚጠጉ የመድሃኒት አይነቶች የሚገኙት ከዚሁ ደን ነው፡፡
•አናኮንዳን የመሳሰሉ አደገኛ የእንስሳት ዝርያዎች የሚገኙት እዚሁ አማዞን ጫካ ውስጥ ነው፡፡
•ደኑ ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ እጽዋቱ ጸሃይ የሚያገኙት ከ2 እስከ 5 በመቶ ብቻ ነው ፡፡
ምንጭ፡ ሲ ኤን ኤን እና የተለያዩ ድረ ገጾች
Comments
Post a Comment