ጎጃም ምድረ_ገነት
ጎጃም ምድረ ገነት
እስኪ ፍቀዱልኝ .........!!!
ልፃፍ ስለ ጎጃም _ ለትውልድ ሀገሬ ፣
ከ'ማሆይ ገላነሽ _ ቅኔን ተበድሬ ፣
ዜማውን ተውሼ _ ከአድማሱ ጀምበሬ ፣
ከሐዲስ አለማየሁ _ ቃላትን ቆጥሬ ፣
ካ'ባኮስትር በላይ _ ጀግንነት ተምሬ ፣
አትነካኩኝ ልፃፍ _ በግጥም ዘርዝሬ ።
......................................................
መሸንቲ ቢኮሎ _ ዱርቤቴ ይስማላ ፣
ዘንዘልማ አዴት _ መራዊ ሰከላ ፣
እጅግ ይጣፍጣል _ እሸቱ ሲበላ ።
ቲሊሊ ኮሶበር _ ቻግኒ እንጅባራ ፣
የሚገበይበት __ የፍቅር እንጀራ ።
ቢቡኝ ድጎ ፅዮን _ ቋሪት ደጋ ዳሞት፣
መለያቸው ድፍረት _ አርማቸው ጀግንነት ።
እነሴና እነብሴ _ ደጄንና አቸፈር ፣
ሸበልና ማርቆስ _ ዳንግላ ባህርዳር ፣
የማርና ቅቤ _ የማኛ ጤፍ ምድር ፣
እንዴት ብዬ ላውራው _ አያልቅም ቢነገር ።
...................................................
ልፃፍ ስለ ጎጃም _ በብጣሽ ወረቀት ፣
ከአቡነ ቴዎፍሎስ _ እንዳገኝ በረከት ፣
ከእምቢ አልወለድም.. ከአቤ ጉበኛ....
................. __ እንድቀስም እውቀት !!!
ከበውቀቱ ስዩም _ ከአለቃ አያሌው ፣
ከኤፍሬም ታምሩ _ ከጂጂ ሽባባው ፣
ከአያልነህ ሙላቱ _ ጌትነት እንየው ፤
ከእነዚህ በሙሉ _ ጥበብ እንድቀዳ ፣
ልፃፍ ስለጎጃም _ ጠዋት በማለዳ።
................................................
ማርቁማ ወይንማ _ ሽንዲ ወንበርማ ፣
የምርት ጎተራ _ የሰብል አውድማ ።
ሞጣ ቀራኒዮ _ ቢቸና ደብረወርቅ ፣
ልባቸው ሩህሩህ _ ፍቅራቸው የማያልቅ ።
አነደድ የጁቬ _ ሉማሜ ጎዛምን ፣
የውቦች ቀዬ ነው _ ያስንቃሉ አለምን።
አማኑኤል ደምበጫ _ ጃቢጠህናን ቡሬ ፣
ጎጃም ውበት አለው _ ለምለም ነው ሀገሬ ።
....................................................
አንቺ የኔ ፍቅር. ...................!
ውሃ ትወጃለሽ _ ሰማሁልሽ ወሬ ፣
ተዘጋጅ ላሳይሽ _ ምን ጎድሎት ሀገሬ።
ወንዝ ከተመቸሽ ...................!
ከአባይ ከምንጩ _ ግዮን ከጠበሉ ፣
ጨሞጋና ፈጣም _ ጎጃም ከመሀሉ ፣
አብያና ጥጃን _ ብርና ላህ አሉ ፣
ጉማራና ተምጫም _ ላንቺ ይበቃሉ ፣
መዋኘት ካማረሽ ................!
ባህረ ጊዮርጊስ _ ገራይ ነው? ዘንገና ፣
ወይስ ከጉደራ _ አልያ ከጣና ፣
የትኛው ሐይቅ ላይ _ ምረጭ እንዝናና ፣
ፍቅሬ ይህ ነው በይኝ _ ልውሰድሽ ልምጣና።
ገዳምም ከፈለግሽ ..................!
ሰኞ ጫቢ ማርያም _ ማክሰኞ ዋሸራ ፣
ሮብ ደብረ ዲማ _ ሐሙስ ከድንግራ ፣
አስጎበኝሻለሁ __ አቅፌሽ በግራ ።
አርብና ቅዳሜ _ ቢቸና ጊዮርጊስ ፣
ናዳ ላይ ተሳልመሽ _ እሑድ ጣና ቂርቆስ፣
ነይና ከጎጃም _ መንፈስሽ ይታደስ ።
ይሄው እንዳየሽው. ...................!
ህዝቡ ያስደምማል _ በደንብ ላስተዋለው፣
ሲነጋገር በአሽሙር _ ቅኔና ዜማ አለው ።
ቡዳ ነህ አትበይኝ ...........!
ቡዳ መንፈስ ሳይሆን _ የሚያምር ፍቅር ነው፣
በጎጃሜ ቋንቋ _ ቡዳነት መውደድ ነው፣
እምጥንተ ፍጥረት _ ከአዳም የወረስነው ።
...............................................
ጎጃም ህቡዕ ነው. ..................!!!
ጎጃም ምስጢር ነው. ..............!!!
ጎጃም ምሉዕ ነው _ አያልቅም ቢነገር፣
የጮቄ ተራራ __ አራት መከራክር ፣
የብር አዳማ ጫፍ _ የአራራት አሳንሱር፣
የአቮላ አቀማመጥ _ የአባ ዳሞ ታምር ።
..............................................
በጋራ ሸንተረር _ የተዥጎረጎረች ፣
ጢስ አባይ ፏፏቴን _ በእቅፏ የያዘች ፣
ጎጃም ሙሽራ ናት _ በጌጥ የደመቀች ።
ይገለጥ መጽሐፉ _ ኦሪት ዘ'ፍጥረት ፣
የሰው ልጅ እስትንፋስ _ የግዮን እናት ፣
መሆኗን ያሳያል _
Comments
Post a Comment