#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_7


#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_7
 #እውትተኛና_አስተማሪ !!!!
በብዙ ችግሮች መሀል ልቡ ዳግም ማፍቀር ችሎ ሰላምን ማፍቀር ቢችልም የራሱ ማድረግ ግን አልቻለም ምክንያቱ ደግሞ ገንዘብ ማጣት ነው ... ይህን ሲያውቅ ወጥቶ ሲጠጣ አመሸ ... ለሊት ላይ ሲመለስ ሰላም ቁጭ ብላ ትጠብቀው ነበር ... ሰላም ከሚያውቃቸው ብዙ ሴቶች ትለያለች ሴት ልጅ ብዙ ነገሩን እንዲያጣ መንስኤ ሆና ልቡን ብትሰብረውም ሰላም ግን ትለያለች ከነ ምንነቱ ተቀብላ ከልቧ ታፈቅረዋለች በብዙ መመዘኛዎች ተመዝና ያለፈች ብቸኛ ሴት ናት ...
ልክ ሲገባ እዛች ጠባብ ክፍል ውስጥ ወንበር ላይ ኩርትም ብላ ትጠብቀው ነበር እማማ ተኝተው ስለነበር ፍቅር እንዳታወራ እማዬን ትቀሰቅሳታለህ አለች ከተቀመጠችበት ተነስታ እሱን ለማስቀመጥ ወደሱ እየተጠጋች እሺ አላወራም የኔ ውድ አለ በተወለጋገደ አማርኛ መስከሩን ለመሸሸግ እየጣረ ሰላምም አቅፋው ታለቅስ ጀመር ... ለምን ጥለኸኝ ታመሻለህ ለምን ትጠጣለህ አስጠላውህ ?ብላ ጠየቀች እሱም እንባው ቁልቁል እየወረደ በፍፁም የኔ ውድ መቼም አታስጠዪኝም ግን በቃ የኔ ላቶኚ ልቤን መስጠቴ አሳሰበኝ አለ ወደደረቱ እያስጠጋት የኔ ፍቅር እኔኮ ሁሌም ያንተ ነኝ አለችና ልትስመው ወደከንፈሩ ስትጠጋ ኧረ እማማ ይነቃሉ ውዴ አላት እሷም ፈገግ ብላ ቅድምኮ አውቄ ነው ሰካራም አይንህ አያይማ እማዬኮ ዛሬ እህቷጋር አዳር ሄዳለች አለችና እጁን ይዛው ወደአልጋው አመሩ ... ፍቅራቸውንም በነፃነት ይለጋገሱ ጀመር ሰላምና ፍፁም አንሶላ ተጋፈፉ የሰላም ድንግል መሆን ለፍፁም ቢገርመውም ክብሯን ለሱ አሳልፋ መስጠቷ ይበልጥ በልቡ ቦታን ሰጣት...
የሁለቱ መዋደድ ግን ከምንም ሊያድናቸው አልቻለም አራጣ አበዳሪው ሰውዬ የመጨረሻ ማስጠንቀቅያ ሰጡ ሰላም ምንምኳ አሻፈረኝ ብትል ለእናቷ ስትል የግድ ማድረግ ነበረባት ... ተለያዩ!
ትጉም አልባ ህይወት መምራት የቀፈፈው ፍፁም እማማ የሺን ተሰናብቶ ወደ ናዝሬት ሄደ ምናልባት አየሩ ሲቀየር ልረሳት እችላለው ብሎ ስላሰበ ነበር ይህን ያረገው...
ሰላም ከሰውየው ጋር መኖር በጀመረች 3ወሯ እናቷ ጋር ስትመጣ አርግዛ ነበር እማማ የሺም ልጃቸውን ለምን ፈጠንሽ ሲሉ ተቆጧት እሷም ያረገዘችው ከሰውየው ሳይሆን ከፍፁም መሆንኑን አልቅሳ ነገረቻት እናትም ሰውየው ይህን ካወቀ ይገልልሻ በዛ ላይ ፍፁም ያለበት አይታወቅም ሲሏት እናትና ልጅ መላቀሳቸውን ቀጠሉ....
#በቀጣይ_መጨረሻው_ይቀጥላል

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች