#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_6


#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_6
 #እውትተኛና_አስተማሪ !!!!
ፍፁም ያባቱን ገዳይ አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት በደምብ እርግጠኛ ለመሆን ሰውየውን አንድ ጥያቄ ጠየቀው ... ምን ጓደኛውን ነው የገደለው አለ ጥያቄው ልክ ይሁንም አይሁን ግድ ሳይሰጠው ይሄኔ ሰውየው አዳማጭ ያገኘለትን ወሬውን ለመሰለቅ እየተዘጋጀ አረቂውን ፉት አለና ... አይ አንተ ሟቹማ ምን ለሱ ብቻ ለኛም የምሽት ጓደኛችን ነበሩ ግን ምን ታረገዋለህ... ሴት ልጃቸውን ገና በለጋ እድሜዋ ተነጠቁ ከዛም ሚስታቸው ተከተለች ይሄኔ አለኝ የሚሉት ወንድ ልጃቸው የት ገባ ሳይባል ጠፋና ብቻቸውን ቀሩ ... ብሎ ንግግሩን ለመቀጠል መለኪያውን አንስቶ ጎንጨት ብሎ ሳይመልሳት ፍፁም ከመቅፅበት ተነስቶ አባቱን ገደለ የተባለውን ሰው በጠርሙስ አናቱን አለው ይሄኔ ሰዎች ተረባርበው ያዙት ...
በደቂቃዎች ልዩነት ፖሊስ አካባቢውን ወረረው ፍፁምንም ጥፋተኛ ብለው አሰሩት ... ይሄኔ ለቀናት ያህል የድሮ ሰፈሩ ሰዎች ተመላልሰው ጠየቁት ነገር ግን ከዛ ቡሃላ ቀሩ ሰውየው በከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል ስለተኛ ምናልባት ከሞተ እንደማይፈታ ተነገረው ... ሁሌም የማትቀረው የማማ የሺ ልጅ ሰላም ነበረች ሁሌም ምግብ ሰርታ ትጠይቀዋለች እማማም አልፎ አልፎ ይመጣሉ... ፍፁም ከታሰረ 3ወር ሞላው ...
ፍፁምን ሰለቸኝ ሳትል የምትጠይቀው ሰላም ሀሳቧ ሁሉ ስለሱ ነው እሱም አሁን ላይ ከሚያውቃቸው ሴቶች ስለተለየችበት ፍቅር የልቡን በር ያንኳኳው ጀምሯል ሰላም ቆንጆ ከመሆንም ባለፈ ብዙ ፈተናን ሊያውም በሰው ሀገር አሳልፋለች ስለዚህ ሰው ያስፈልጋታል ለዛም ነው ፍፁም ለሷ ለየት ያለ ስሜት ያደረበት... ልክ በሶስተኛው ወር ሰውየው እስኪድን ድረስ ሊያሳክም ፈርሞ ተፈታ ይሄኔ ከሱ በላይ እማማና ሰላም ተደሰቱ...
ይህ በንዲህ እንዳለ ፍፁም ሰውየውን ማሳከም ጀመረ ከስራ መልስ ከሰላም ጋር ወክ ያረጋሉ ከዛም አልፎ ቤተክርስትያን ይሄዳሉ በዚ ሰአት የፍቅር ጥያቄ አቅራቢ ሳይኖር ፍቅር ተጀመረ እማማ የሺም ሁለት ልጅ ስላላቸው ሁሌም ፈጣሪን ማመስገን ቀጠሉ... ታድያ የፍፁምና ሰላም ደስታ ከቀናት አልዘለለም ... የሰላም አባት ሳይሞቱ በፊት የነበረባቸውን እዳ በልጃቸው ቀይረው ኖሩ አራጣ አበዳሪው አቶ ግርማ የሰላምን መምጣት ሲሰሙ ግዜ ሳያጠፉ ሰላምን ለመውሰድ እማማ የሺን ያስጨንቋቸው ጀመር ይሄኔ ፍፁምን ብቻውን እንደሚፈልጉት ነግረው...
ልጄ እህትህን ሰላምን ሊነጥቁኝ ነው ያለእኩያዋ የማትፈልገው ህይወት ውስጥ ልትገባብኝ ነው ወይ እሷን መስጠት ወይ ከነወለዱ እዳውን መክፈል ግድ ነው እዳውን መክፈል መሞከር ደግሞ የማይታሰብ ነው ሲሉ አለቀሱ ምንም ሳይላቸው ትቷቸው ወጣ እድል ይሁን እጣ ፈንታ ብቻ ፍፁም የኔ ያላቸውን ሰዎች ሁሌም ይነጠቃል... 
#ይቀጥላል...

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው