#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_5
#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_5
#እውትተኛና_አስተማሪ
!!!!
ፍፁም አባቱንም እናቱንም በራሱ ቸልተኝነት አጣ አባቱን ማን ሊገልበት ይችላል? መገመት እንኳን አይችልም... ጎረቤቶቹም ፍፁምን አረጋግተው ከሰአታት ቡሃላ ተቀመጠ ይሄኔ አንድ የቅርብ የነበሩ ጎረቤት እምባቸውን በነጠላቸው ጠራርገው ልጄ አባትህ ምንም ጠላት አልነበራቸውን ብቻ አንተ ጥለሃቸው ስቴድና ሚስታቸው ማለቴ እናትህንም በሞት ሲያጡ ብቸኝነቱን ለመርሳት አብዝተው ይጠጡ ነበር ይሄኔ አንድ ለሊት ሰክረው ወደቤት ሲጓዙ እንደሳችቸው መጠጥ አቅሉን ያሳጣው ሰው በማይረባ ምክንያት ተጣልተው ሲገፈትረው አጋጣሚ አባትህ ድንጋይ ላይ ወድቆ አጉል ቦታ ስለተመታ በዛው ህይወቱ አለፈ... አሉና እምባቸው ነጠላቸውን እስኪያርሰው ድረስ ይወርድ ጀመር...
ፍፁም ህይወት በጣም ቀፈፈችው ... ያባቱን ገዳይ ቢፈልግም ከፖሊስ እስከ ሰፈር ሰው አውቃለው የሚለው ጠፋ ስለዚም በራሱ መንገድ ሰውየውን ለመፈለግ ወስኖ ወደ እማማ የሺ ተመለሰ ከወጣ በመቆየቱ አይመለስም ብለው ተስፋ የቆረጡት ሴትዮ ልክ ሲያዩት ልክ እንደ ልጅ በደስታ ቦረቁ ከዛም ደሞ ፊቱ ላይ ሀዘን አይተው ወድያው አንድ ነገር ከፊቱ ያነበቡ መሰላቸው ልጄ አባትህ ደና አይደሉም አሉት በስስት እየተመለከቱ ፍፁምም ከንግግሩ እምባው እየቀደመ እማማ አባቴኮ ሞተ በባዶ ቤት ውስጥ ማንም የሚረዳው እቶ በመጠጥ ተቃጥሎ አባቴ በስተመጨረሻ በሰው እጅ ሞተ አለ... እማማ የሺ የራሳቸውን ሀዘን ሸሽገው ፍፁምን አፅናኑት
ይህ በሆነ በሳምንቱ የማማ የሺ ልጅ ሰላም በጎረቤት ስልክ ደውላ ወደ ኢትዮጵያ ልትመጣ መሆኑ ተሰማ እስከዛሬ ትኑር ትሙት የማትታወቀው ሰላም ልትመጣ መሆኑን ሲሰሙ እማማ የሺ በህልማቸው ነበር የመሰላቸው ባጋጣሚ ላናገራቸው ሁሉ ስለልጃቸው ነበር ወሬአቸው ....ፍፁምም የአባቱን ገዳይ አግኝቶ ለመበቀል ሁሌም ማታ አባቱ ይጠጣበት የነበረው ግሮሰሪ ይሄድና የዛን ቤት የረጅም ግዜ ጠጪዎች ጆሮ ይጠባል....
ይህ በንዲህ እንዳለ ሰላም ከአረብ ሀገር መጣች በእውነቱ ስትመጣ ይህን ያህል አመት ሰው ሀገር ብትቆይም ባዶ እጇን ነበር የመጣችው እማማ የሺም ልጃቸው ምንም አለማትረፏ አልታያቸውም በህይወት መገናኘታቸውን ብቻ ነበር የሚፈልጉት ... እማማ የሺም ልጃቸው ሰላምን ከፍፁም ጋር አስተዋወቋት ሰላም ልክ እንዳየችው ልቧ ደነገጠ በፍቅር አይን ተመለከተችው እሱ ግን በወንድምነት አይኑ ነበር ያያት... ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ምሽት እንደለመደው መጠጥቤት ሄዶ ተቀመጠና ይጠጣ ጀመር ይሄኔ አንድ በእድሜ ገፋ ያለ ሰው ያዋራው ጀመር መጀመርያ ፍፁም ሰውየው የሚያወራውን ከምንም አልቆጠረውም ነበር ከዛ ግን አንድ ንግግር ትኩረቱን ሳበው አየኸው እንዴት እንደሚያረገው በዚ እድሜው እንዲ ሲቅለበለብ ነው ምስኪኑን ሰውዬ ገፍትሮ እንዲሞት ያረገው ... አሉ ሰውየው ይሄኔ ልቡ ስንጥቅ አለ ያባቱን ገዳይ ፊት ለፊት አገኘው...
#ይቀጥላል...
#ይቀጥላል...
Comments
Post a Comment