#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_4


#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_4
 #እውትተኛና_አስተማሪ !!!!
ፍፁም ከሰአታት ቡሃላ ሲነቃ አንዲት እናት ካጠገቡ ተቀምጠዋል የት እንዳለ ለማወቅ በዙርያው ተመለከተ አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ብዙም ኮተት ያልበዛባትና እንዲሁ በግምት የአቅመ ደካማ መኖርያ ውስጥ ነው የተኛበት ፍራሽ ከመሳሳት አልፎ አንሶላ ሆንዋል ሴትየዋ ገና ከመንቃቱ የናትነት አንጀታቸው ክፉኛ ማዘኑን እያሳበቀባቸው ተመስገን ጌታዬ ነቃህ ይኔ ልጅ አሉ ደሙን የጠራረጉበትን ጨርቅ ለመሸሸግ እየሞከሩ ... በስስት አያቸው እናቱን አስታወሰ ... አይኑ ላይ ክርትት አለበት የናቱ ምስል ይሄኔ አይኖቹ እምባ አቀረዘዙ...
ሴትየዋም ልጄ ገንዘብ ስላልነበረኝ ነው ሀኪም ዘንድ ያሎሰድኩህ እዚ እበሬ ላይ ጥለውክ ሂደው እኮ ነው ግን ምን አይነት አረመኔዎች ናቸው ብለው የሱን መልስ ሳይጠብቁ በክሰል ወደጣዱት ድስት አመሩ ጥቂት ቆይተውም በኩባያ አጥሚት ይዘውለት መተው ጎሽ ልጄ ተነስ እቺን ጠጣ ከዛ እጅህን አሽልሃለው አሉት። ሰአቱ ጨለምለም እያለ ነው ፍፁምም እኚን ፈጣሪ የላካቸው መላክ በስስት እያየ ተነስቶ አጥሚቱን ጠጣ ከዛም እኔም እንደርሶ እሩሩህ እናት ነበረችኝ አለ አቀርቅሮ ምድር እየተመለከተ ከዛስ አሉ እጃቸውን በጉንጫቸው ላይ አኑረው ገደልኳት አለ በፀፀት ውስጡ እየበገነ ይሄኔ ሴትየዋ ስብአት ለአብ ብለው አማተቡ ልጄ እውነትህን ነው አሉ አዎ እማማ ያኔ እኔ ብር ባልሰርቃት ታክማበት ትድን ነበር ያኔ እኔ እናቴን በዛች ሰይጣን ከሀዲ ባልቀይራት እናቴ አትሞትብኝም ነበር... እያለ ያለቅስ ጀመር ሴትየዋም ልጄ ተረጋጋና የሆነውን አውራኝ እስቲ አሉት...
ሁሉንም ነገር ነግሮአቸው ሲያበቃ ይሄ ነው እማማ የተደበደብኩትም በሀጥያቴ ነው አለ ከዛም ቤት ውስጥ ለጥቂት ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ ሴትየዋም ለፍፁም አጥንት የሚያለመልም ምክራቸውን ለገሱት አባቱንም እየሄደ መጠየቅ እንዳለበት ነገሩት እስከዚያው ግን እሳቸው ጋር እስከፈለገበት ግዜ ድረስ ቢኖር ደስ እንደሚላቸው ነገሩት ፍፁምም ተስማማ እናት ማግኘቱ ደስ እያለው ... እማማ ግን እርሶ ልጅ የሎትም? አለና ጠየቀ...
እምማ የሺ ነው ስማቸው ልጅም ነበራቸው አንዲት እምቡጥ የምታሳሳ ግን 15 አመቷ አረብ ሀገር ካሌድኩ ብላ ሄዳ እስከ ስድስት ወር አለው እያለች ብደውልም ከዛ ቡሃላ ግን ድምጿ እንደጠፋባቸው እያነቡ ነገሩት እሱም አይዞት ትገኛለች ብሎ አፅናናቸው... ፍፁም ከተከራየበት ቤት ወቶ ከማማ የሺ ጋር መኖር ጀመረ ስራም ልምድ ስለነበረው ተመልሶ ሌላ ቦታ ተቀጠረ...
ከወራት ቡሃላ እማማ የሺ አደፋፍረውት አባቱን ለመጠየቅ ወደ ጨርቆስ ሄደ ልክ ሊደርስ ሲል ልቡ በፍርሃት እራደ እየቀፈፈው እዛች ደሳሳ ጎጆ ደረሰ ግን ቤቷ ዝግ ነበረች ይሄኔ አባቱን ለመጠበቅ የእናቱ ቡና አጣጭ የነበሩት አስካለ ጋር ጎራ አለ እትዬ አስካለም ገና ሲያዩት አይናቸው እምባ አቀረረ ... ትንሽ ካወሩ ቡሃላም ያባቱን በሰው እጅ መገደል አረዱት ... ይሄኔ ያባቴ ገዳይ ማነው ሲል መንደሩን በጩኸት አደባለቀው...
#ይቀጥላል...

Comments

Popular posts from this blog

የግዕዝ ምሳሌያዊ አነጋገሮች

ግዕዝና አማረኛ ዓለም አቀፍ ናቸው