#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_3
#የተጎዳ_ልብ_ክፍል_3
#እውትተኛና_አስተማሪ !!!!
ከፍፁም ያረገዘችው ሳሮን ፍፁም ሲክዳት የራሷን እርምጃ መውሰድ ጀመረች በቅድምያ የሚሰራበት ጋራጅ ድረስ በመሄድ በአባቷ አስጠየቀችው ፍፁም ግን ልጆትን የትም አላውቃትም ሲል ሸመጠጠ
... በዚ የተከፋችው ሳሮን ዳግም ፊቱ ቆማ ላትለምነው ወስና ሄደች ... ሳሮን ምንም እንኳ የሀብታም ልጅ ብትሆንም ይህን ግን መቋቋም አቃታት ልጇ ቢወለድ ያላባት ፍቅር ማደጉ ሳያንስ ሳሮን ፍፁምን በጣም ታፈቅረዋለች እሱን አቶ መኖር ከበዳት...
ከቀናት ቡሃላ ፍፁም አገር ሰላም ብሎ ወደ ስራው ገብቶ ሳለ የሳሮን አባት ጥቁር ልብሳቸውን ለብሰው ብቻቸውን እያወሩ መጡ እውነት ለመናገር ሁኔታቸው ያስፈራል ሁሉም ስፕራተኞች ደንግጠው ቆሙ ይሄኔ ፍፁም የእናቱ ሞት ሀዘን ባደነደነው ልቡ ቀና ብሎ አይቷቸው ብቻ ወደስራው ተመለሰ
የሳሮን አባትም ና ውጣ አንተ ሴሰኛ የልጄ መሞት ምክንያት አንተ ነህ ደስ ይበልክ ይሄው እራሷን አጠፋች አሁን ምን ልታረግ ነው ድግስ ደግሰህ የመሞቷን ደስታህ ታከብራለህ? ንገረኝ ልጄን ለምን እንድትሞት ፈረድክባት ላንተ ግዚያዊ ስሜት ብለህ ለምን ... ብለው መሬት ላይ ተደፍተው የልጃቸውን ስም እየጠሩ ያለቅሱ ጀመር እሳቸውን አይቶ አብሮ ያላለቀሰ አልነበረም....
የሳሮን አባትም ና ውጣ አንተ ሴሰኛ የልጄ መሞት ምክንያት አንተ ነህ ደስ ይበልክ ይሄው እራሷን አጠፋች አሁን ምን ልታረግ ነው ድግስ ደግሰህ የመሞቷን ደስታህ ታከብራለህ? ንገረኝ ልጄን ለምን እንድትሞት ፈረድክባት ላንተ ግዚያዊ ስሜት ብለህ ለምን ... ብለው መሬት ላይ ተደፍተው የልጃቸውን ስም እየጠሩ ያለቅሱ ጀመር እሳቸውን አይቶ አብሮ ያላለቀሰ አልነበረም....
ይሄኔ ፍፁም ካቀረቀረበት ቀና ብሎ እኔ ለግዜአዊ ስሜት ኖሬ አላውቅም ግን የኔ ትምህርት መቋረጥና ከምንም በላይ በምድር የምታስፈልገኝን እናቴን ያጣሁበት ምክንያት ሴት ናት ለሴት ልጅ አላዝንም በጥቅም እንጂ በፍቅር ለማታምን ሴት አላዝንም ብሎ እንባውን እያዘነበው ከነስራ ልብሱ ወቶ ሄደ...
ይህ በንዲህ እንዳለ ከ3 ቀን ቡሃላ ተመልሶ ወደ መስሪያ ቤቱ ተመለሰ ይሄኔ ግን አለቃው አባረሩት ፍፁምም በብስጭት ወቶ ወደመጠጥ ቤት ሄደ የሚገርመው አንድ እንኳ ጓደኛ አይፈልግም ብቻውን ተቀምጦ ሲጠጣ ከቆየ ቡሃላ ተነስቶ ሲወጣ ሞቅ ብሎት ነበር ይሄኔ ሁለት በእድሜም በቁመትም በሰውነትም የሚበልጡት የሚመስሉ ወንዶች አስቆሙት ከዛም ባልጠበቀው መንገድ ነገር ፈለጉት እሱም መጠጥ ያደፋፈረው ወንድነቱ እየተፈታተነው ገፍትሮዋቸው ሊሄድ ሲል ሁለቱም እኩል በሰነዘሩት ቡጢ ዘረሩት ከዛም እዛው በወደቀበት ቀጥቅጠውት ሄዱ...
ማንም የሌለው ፍፁም ራሱን ስቶ እንደወደቀ ሰአታት አለፋ...
#ይቀጥላል...
#ይቀጥላል...
Comments
Post a Comment